በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኔታንያሁ በእስራኤል ምርጫ ቀደም ብሎ እንዲካሄድ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረጉ


በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ምርጫ ቀደም ብሎ እንዲካሄድ ለመጠየቅ፣ በእስራኤል፣ ቴላቪቭ ባደረጉት ሰልፍ፣ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት አያያዛቸው ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል
በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ምርጫ ቀደም ብሎ እንዲካሄድ ለመጠየቅ፣ በእስራኤል፣ ቴላቪቭ ባደረጉት ሰልፍ፣ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት አያያዛቸው ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል

በሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን በቴል አቪቭ ፀረ-መንግስት ተቃውሞ እያደረጉ ባሉበት ወቅት፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ምርጫው ቀደም ብሎ እንዲካሄድ የሚጠይቀውን ሀሳብ ውድቅ አድርገዋል።

እ.አ.አ ጥቅምት ሰባት ሐማስ ያደርሰው የሽብር ጥቃት በጋዛ እና በእስራኤል መካከል የሚካሄደውን አውዳሚ ጦርነት ከቀሰቀሰ ወዲህ፣ ኔታንያሁ የነበራቸው ተቀባይነት አሽቆልቁሏል።

እ.አ.አ በ2023 ሀገሪቱን ያናወጡ ፀረ-መንግስት ተቃውሞዎች በጦርነቱ ምክንያት ጋብ ብለው የነበረ ሲሆን፣ አሁንም ሰልፈኞች ቅዳሜ ምሽት በቴል አቪቭ ጎዳናዎች ላይ ሰልፍ በማድረግ፣ በ2026 መካሄድ ያለበት ምርጫ ቀደም ብሎ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ ቢሆንም፣ ባለፈው አመት ይደረጉ ከነበሩ ሰፊ ተቃውሞዎች ያነሰ ቁጥር መሆኑ ተገልጿል።

ከተቃዋሚዎቹ አንዱ የእስራኤልን ባንዲራ እያውለበለ ባስተላለፈው መልዕክት "ለመንግስት ማለት የምፈልገው ጊዜያችሁን ተጠቅማችኃል፣ ልታጠፉ የምትችሉትን ሁሉ አጥፍታችኃል። አሁን ህዝቡ እናንተ ያበላሻችሁትን የሚያስተካክልበት ሰዓት ነው" ሲል ተናግሯል።

ኔታንያሁ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት፣ ምርጫ ቀደም ብሎ እንዲደረግ ስለቀረበው ጥያቄ ተጠይቀው "በአሁኑ ሰዓት የምንፈልገው የመጨረሻው ነገር፣ ምርጫ ነው። ምክንያቱም ምርጫ ይከፋፍለናል" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG