በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒው ዮርክ ትውልደ ኢትዮጵያዊቱ ቤተ እስራኤላዊት ዕጩ ተፎካካሪ የቀረቡበት ማሟያ ምርጫ እየተካሄደ ነው

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባል ዲሞክራቱ ታም ሱዋዚ ከትውልደ ኢትዮጲያዋ ቤተ እስራኤላዊት የናሷ ወረዳ ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባል ጋር እየተፎካከሩ ናቸው።
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባል ዲሞክራቱ ታም ሱዋዚ ከትውልደ ኢትዮጲያዋ ቤተ እስራኤላዊት የናሷ ወረዳ ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባል ጋር እየተፎካከሩ ናቸው።
የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባል ዲሞክራቱ ታም ሱዋዚ በኒው ዮርክ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ።
የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባል ዲሞክራቱ ታም ሱዋዚ በኒው ዮርክ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ።

ከዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የተባረሩትን የኒው ዮርኩ ሪፐብሊካን አባል ጆርጅ ሳንቶስ መቀመጫ ለመያዝ የተጋጋለ ፉክክር ሲደረግበት በከረመው ምርጫ መራጮች ዛሬ ማክሰኞ ድምጽ እየሰጡ ነው።

በኒው ዮርክ ከተማ አቅራቢያ የሎንግ አይላንድን እና የተወሰነ የኩዊንስ አካባቢን ሊሚጠቀልለው የ3ኛ ወረዳ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት መቀመጫ የሚካሄደው ልዩ ምርጫ ምክር ቤቱን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለው ፉክክር ምን ያህል የተጧጧፈ እንደሆነ ያመላክታል።

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባል ዲሞክራቱ ታም ሱዋዚ ከትውልደ ኢትዮጲያዋ ቤተ እስራኤላዊት የናሷ ወረዳ ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባል ጋር እየተፎካከሩ ናቸው።

የአስራ ሁለት ዓመት ታዳጊ ልጅ ሳሉ እስራኤል 14 ሺህ አምስት መቶ የሚሆኑ ቤተ እስራኤላውያንን በወሰደችበት ዘመቻ ሰሎሞን በተባለው ጉዞ ወደእስራኤል የተጓዙት ማዚ ፒሊፕ በእስራኤል የጦር ሠራዊት ውስጥ አገልግለዋል። በኋላም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2005 ዓ.ም ከዩክሬናዊ አሜሪካዊው ሐኪም ባለቤታቸው ጋር ትዳር መስረተው ወደ አሜሪካ የመጡ ሲሆን በ 2021 ዓም የኒው ዮርክ ናሷ ወረዳ ምክር ቤት አባል ሆነው ተመርጠዋል።

የአስራ ሁለት ዓመት ታዳጊ ልጅ ሳሉ እስራኤል 14 ሺህ አምስት መቶ የሚሆኑ ቤተ እስራኤላውያንን በወሰደችበት ዘመቻ ሰሎሞን በተባለው ጉዞ ወደእስራኤል የተጓዙት ማዚ ፒሊፕ፣ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የካቲት 5/2024 ኒው ዮርክ ውስጥ በገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ።
የአስራ ሁለት ዓመት ታዳጊ ልጅ ሳሉ እስራኤል 14 ሺህ አምስት መቶ የሚሆኑ ቤተ እስራኤላውያንን በወሰደችበት ዘመቻ ሰሎሞን በተባለው ጉዞ ወደእስራኤል የተጓዙት ማዚ ፒሊፕ፣ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የካቲት 5/2024 ኒው ዮርክ ውስጥ በገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ።

መሀል ክረምት ላይ ያልተለመደ የሆነው ምርጫ እንዲካሄድ ግድ የሆነበት ምክንያት ሪፐብሊካኑን ጆርጅ ሳንቶስን ባለፈው ታህሳስ የአባልነት ዘመናቸውን እንዳጋመሱ በመባረራቸው ነው።

ሳንቶስ ዲሞክራቲክ ፓርቲው አስተማማኝ የመራጭ ድጋፍ ባለው ወረዳ ለመመረጥ በሀሰት ራሳቸውን ከወዛደር የውጭ ሀገር ሰዎች ተወልደው በዎል ስትሪት የፋይናንስ ገበያ ለከፍተኛ ስኬት ያበቁ አሜሪካዊ አድርገው በማቅረብ ተወንጅለዋል።

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባል ዲሞክራቱ ታም ሱዋዚ በኒው ዮርክ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባል ዲሞክራቱ ታም ሱዋዚ በኒው ዮርክ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ

ስለራሳቸው ያቀረቡት አብዛኛው ታሪክ ሀሰት መሆኑ ከተመረጡ በኋላ የተጋለጠ ሲሆን ከሪፐብሊካን ፓርቲው የደጋፊዎች መዋጮ ገንዘብ መስረቅን ጨምር በርካታ ክሶች ተመስርተውባቸዋል።

ዲሞክራቱ ተፎካካሪ ታም ሱዋዚ ካሁን ቀደም ሦስት ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የኒው ዮርክ ወረዳ 3 ተወካይ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ የምረጡኝ ዘመቻቸው ሎንግ አይላንድ ውስጥ የህዝብ ድጋፍ ከሌላቸው ተራማጅ ፖሊሲዎች በመራቅ ከሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ጋር መሥራት እንደሚችሉ ሲናገሩ ቆይተዋል።

ማዚ ፒሊፕ ሪፐብሊካን እንደሆኑ በይፋ ያስታወቁ እና ለወረዳ ምክር ቤት የተመረጡትም በሪፐብሊካን ፓርቲው ስም ይሁን እንጂ የተመዘገቡ የዲሞክራቲክ ፓርቲው አባል ናቸው።

ይህን ጉዳይ ሲያብራሩ ዲሞክራቲክ ፓርቲውን የተቀላቀሉት አሜሪካ እንደመጡ መሆኑን እና እየቆዩ ፓርቲው በይበልጥ ግራ ዘመም ተራማጅ ፖለቲካ እያቀነቀነ ሲሄድ ከፓርቲው እየራቁ መምጣቸውን ተናግረዋል። ከምርጫው በኋላ የፓርቲ አባልነታቸውን እንደሚቀይሩ ቃል አቀባያቸው አስታውቀዋል።

ማዚ ፒሊፕ ራሳቸውም በአንድ ወቅት ፍልሰተኛ የነበሩ ሁነው ሳለ ዲሞክራቱን ተፎካካሪያቸውን ታም ሱዋዚን እና ፕሬዚደንት ጆ ባይደንን የኢሚግሬሽን ፖሊሲያቸውን በተመለከተ ብርቱ ነቀፌታ ሲያወርዱባቸው ተሰምተዋል።

ሱዋዚም ጽንስ ማስወረድ አሁንም በሕግ የተጠበቀ መብት በሆነባት በኒውዮርክ "ያ መብት እንዳይነካ ይከላከላሉ ተብለው አይታመኑም" በማለት ማዚ ፒሊፕን ነቅፈዋቸዋል።

ከምርጫው በፊት ባደርጉት ክርክር ስዋዚ ፒሊፕን በጽንስ ማስወረድ ጉዳይ አቋማቸውን እንዲያስረዱ ሲጠይቋቸው "ዲሞክራቶች በዚህ ጉዳይ ላይ ስለ እኔ ውሸት ያወራሉ" በማለት ቀጥተኛ መልስ ሳይሰጡ ቀርተዋል።

ዲሞክራቶች የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት መቀመጫውን መልሰው ለመያዝ ለታም ስዋዚ የምርጫ ዘመቻ ብዙ ገንዘብ አውጥተዋል። በቅርብ ጊዜያት ሎንግ አይላንድ ውስጥ በተካሄዱ ምርጫዎች በብዛት ሪፐብሊካኖች እያሸነፉ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG