በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጓንታናሞ ቤይ ታስረው የቆዩ ሁለት የአፍጋኒስታን ዜጎች ተፈቱ


 አብዱል ዛሂር ሳብር እና አብዱል ከሪም የተባሉት እስረኞች ካቡል አየር ማረፊያ በካቡል፣ አፍጋኒስታን፣ እአአ 12/2024
አብዱል ዛሂር ሳብር እና አብዱል ከሪም የተባሉት እስረኞች ካቡል አየር ማረፊያ በካቡል፣ አፍጋኒስታን፣ እአአ 12/2024

እ.ኤ.አ. ከ2002 ጀምሮ ለ14 ዓመታት በጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት በኋላም ከተላለፉበት የኦማን የቤት ውስጥ የቁም እርስ የተለቀቁ ሁለት የአፍጋኒስታን ዜጎች በነጻ መሰናበታቸውን የታሊባን ቃል አቀባይ ትናንት እሁድ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

አብዱል ዛሂር ሳብር እና አብዱል ከሪም የተባሉት እስረኞች የተለቀቁት “በአፍጋኒስታን እስላማዊ ኢሚሬት ጥረት ነው” ሲሉ የታሊባኑ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አብዱል ማቲን ቃኒ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ሰዎች በጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት የቆዩት እኤአ እስከ 2017 ድረስ ሲሆን ቀጣዩን ሰባት ዓመት በእስር የቆዩት የቤት ውስጥ የቁም እስረኛ በሆኑበት የባህረ ሰላጤ ግዛት በሆነችው ኦማን ውስጥ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በኩባ ጓንታናሞ ቤይ የሚገኘውን የማቆያ ማእከል የከፈተችው ከመስከረም 11ዱ (ከ9/11) የሽብር ጥቃት እና የአልቃይዳ መሪ ኦሳማ ቢን ላደን ለመያዝ ከተካሄደው የአፍጋኒስታን ወረራ በኋላ በፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ አስተዳደር መሆኑ ይታወሳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG