በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮትዲዮቫር  የአፍሪካን ዋንጫ በድል አነሳች 


ለአንድ ወር ለተጠጋ ጊዜ ሲከናወን የቆየውን የአፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ዋንጫ ፍልሚያ አዘጋጇ ሀገር ኮትዲዮቫር በአሸናፊነት አጠናቃለች ።
ለአንድ ወር ለተጠጋ ጊዜ ሲከናወን የቆየውን የአፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ዋንጫ ፍልሚያ አዘጋጇ ሀገር ኮትዲዮቫር በአሸናፊነት አጠናቃለች ።

ለአንድ ወር ለተጠጋ ጊዜ ሲከናወን የቆየውን የአፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ዋንጫ ፍልሚያ አዘጋጇ ሀገር ኮትዲዮቫር በአሸናፊነት አጠናቃለች። በፍጻሜው ኮትዲዮቫር ተፎካካሪዋ ናይጄሪያን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዘንድሮ የአፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ዋንጫ ቻምፒዮን መሆኗን አረጋግጣለች።


በ38ኛው ደቂቃ ዊሊያም ትሮስት ኢኮን በአስቆጠራት ግብ ናይጄሪያ መሪነቱን ለመያዝ ችላ ነበር ። ከእረፍት መልስ ተጠናክረው የገቡት የአይቮሪኮስት ተጨዋቾች በናይጄሪያን ቡድን ላይ ጫና በመፍጠር ያከታተሏቸው የግብ ሙከራዎች የቡድኑን የድል መንገድ አቅንተውታል ። በ62ኛው ደቂቃ ውጤቱን ወደ አቻነት የቀየረውን ግብ ፍራንክ ኬሲ ሲያስቆጥር ሴባስቲያን ሀለር በ81ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ሁለተኛ ግብ የኮትዩቫርን ድል አጽንታለች ። በአውሮፓዊያኑ 1992 እና 2015 ካስመዘገበችው የአፍሪካ ዋንጫ ቻምፒዮንነት ታሪክ ጋር የዛሬው ድል ኮትዲቫር ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ በድል ያነሳች የአህጉሩ የእግር ኳስ ዘርፍ ገናና ሀገር አድርጓታል።


ከ60ሺ በላይ ህዝብ በሚያስተናግደው አላሳን ዋተራ (ኢቤምፒ) ስታዲየም የተከናወነውን የፍጻሜ ጨዋታ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ አፍሪካዊያን በቀጥታ ስርጭት ተከታትለውታል ። በዚህ ጨዋታ ወቅት በአትላንታ ኦሎምፒክ ናይጄሪያ በእግር ኳስ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ እንድትሆን ያስቻላት ቡድን አባል ንዋኩ ካኑ እንዲሁም የኮትዲዮቫር ዓለም አቀፍ ኮከብ ዲዲየር ድሮግባ ስታዲየሙን ከአፍ አስከ ገደቡ ከሞላው ኳስ አፍቃሪ ጋር በመቀላቀል ቡድኖቻቸውን ሲያበረታቱ አምሽተዋል ።


የዘንድሮውን የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ለማዘጋጀት 1 በሊየን ዶላር ገደማ እንዳወጣች የተነገረለት ኮትዲዮቫር ፣ በአህጉሪቱ የስፖርት መዘጋብት ላይ በወርቅ ቀለም የሚጻፍ ድል በማስመዝገብ የህዝቦቿን ልብ በደስታ እና በኩራት አፍክታለች ።

የአይቮሪኮስት ተፎካካሪ የነበረችው የሶስት ጊዜ ቻምፒዮን ናይጄሪያ የሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ ፣ በትናንትናው ዕለት በፍጹም ቅጣት መለያ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ያሸነፈችው ደቡብ አፍሪካ የሶስተኛኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀለች ።

በዘንድሮው ውድድር የኢኮቶሪያል ጊኒው ኢሚሊዮ ነሱ 5 ግቦችን በማስቆጠር የኮከብ ግብ አስቆጣሪ የወርቅ መጫሚያ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል ፣ የደቡብ አፍሪካ ግብ ጠባቂ ሮንዊን ዊሊያምስ ምርጥ ግብ ጠባቂ ክብርን ሲያገኝ ፣ ናይጄሪያዊው ዊሊያም ትሮስት ኢኮን ምርጥ ተከላካይ መስመር ተጫዎች ሽልማትን ተቀብሏል።


የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ፓትሪስ ሞስፔ በየደረጃው ድል ላስመዘገቡ ቡድኖች የሜዳሊያ ሽልማት ከመስጠታቸው በተቻሪ ፣ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ጂያኒ አንፋንቲኖ እና የኮትዲዮቫር ፕሬዚደንት አላሳን ዋታራ ጋር በመሆን ደግሞ ለአፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ቻምፒዮኖቹ ፣ ለ"ዝሆኖቹ" ወርቅ የተለበጠውን ዋንጫ አስረክበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG