የእስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሊባኖስ ደቡባዊ የወደብ ከተማ ሲዶን ላይ ጥቃት ፈጸሙ። በጥቃቱ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ በትንሹ ሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የደህንነት ሃላፊዎች አስታውቀዋል።
የእስራኤል የድሮን ጥቃት የተፈጸመው በመካከለኛው ምስራቅ በእስራኤል እና በሀማስ መካከል የተጀመረው ጦርነት በሦስት የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ላይ ከተፈጸመ፣ በሰሜናዊ ምስራቅ ዮርዳኖስ እና እና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ ግጭት እየተካሄደ ባለበት እና በኢራን በሚደገፉ የየመን አማጺያን በቀይ ባህር በሚተላለፉ መርከቦች ጥቃት እየፈጸሙ ባለበት ወቅት ነው።
ትላንት ማምሻውን የእስራኤል ሀይሎች ደቡባዊ የሊባኖስ መንደር በሆነችው ሃውላ ከመስጂድ በመውጣት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሌሎች ዘጠኝ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። በድሮን ጥቃቱም በመስጂዱ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ህጻናት መጎዳታቸውም ተገልጿል።
መድረክ / ፎረም