የሪፐብሊካን እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት የቀድሞው የዩናይት ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ቅዳሜ ዩናይትድ ስቴትስ ለውጭ ሀገራት በምታደርጋቸው ድጋፎች ዙሪያ ሲናገሩ፤ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት በነበሩበት ወቅት የሰሜን አትላንቲክ ጦር አባል ሀገራት ሆነው ለኔቶ የአባልነት ክፍያ በማይከፍሉ ሀገራት ላይ “ሩስያ የፈለገችውን እንድትፈጽም አበረታታለሁ” ብዬ ነበር በማለት ተናገሩ።
በትላንትናው ዕለት ትራምፕ ደቡብ ካሮላይና ኮንዌየ በደጋፊዎቻቸው ፊት ባደረጉት ንግግር ማንነታቸውን ግልጽ ላላደረጉት የኔቶ አባል ይኸንን ማለታቸውን ገልጸዋል። የኔቶ አባል ሀገራት በጎርጎርሳዊያኑ 2014 ሩሲያ ከዩክሬን ላይ ክሬሚያን ጠቅልላ ስትወስድ አባል ሀገራቱ ከዓመታዊ ገቢያቸው ላይ ሁለት በመቶ የሚሆነውን ለኔቶ ያዋጣሉ የሚለው እና በቀዝቃዛው የአለም ጦርነት ወቅት ቆሞ የነበረው የኔቶ የመዋጮ ህግ በድጋሚ እንዲጀምር ማጽደቃቸው ይታወሳል፡።
የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ አንድሪው ቤትስ “በቅርብ አጋሮቻችን ላይ ገዳይ የሆነው አስተዳደር ወረራ እንዲፈጽም ማበረታታት በአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት፣ በአለም መረጋጋት እና በሀገር ውስጥ ምጣኔ ሀብት ላይ አስከፊ እና አስደንጋጭ ተጽዕኖ አለው” ሲሉ ተናግረዋል።
መድረክ / ፎረም