በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ ወታደራዊ ጣቢያ በተፈጸመ ጥቃት አምስት ወታደሮች ሞቱ


ሶማሊያ
ሶማሊያ

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሹ በሚገኝ የወታደሮች ካምፕ ላይ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ አምስት የሚሆኑ የሶማሊያ እና የተባበሩት አረብ ኤመሬት ወታደሮች መሞታቸውን የጦር ሰራዊት አባላት እና የሆስፒታል ሰራተኞች ለሮይተርስ ተናግረዋል።

የተባበሩት አረብ ኤመሬት የመከላከያ ሚኒስቴር የሶማሊያ ወታደሮችን በማሰልጠን ላይ የነበሩ ሦስት የኤመሬት ወታደሮች እና አንድ የባህሬን ወታደር “በሽብር ጥቃት” ተገድለዋል፤ ያለ ሲሆን በተጨማሪም ሌሎች ሁለት ተጎድተዋል ሲል በመግለጫ አስታዉቋል።

እራሱን አህመድ ብቻ ሲል የስተዋወቀ ሰው ታጣቂዎቹ የተባበሩት አረብ ኤመሬት ስልጠና በምትሰጥበት በጎርደን ወታደራዊ ጣቢያ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን አስታውቆ፤ በተጨማሪም ስልጠናውን የጨረሰ ምልምል የሶማሊያ ወታደር ተተኩሶበት መገደሉን ተናግሯል።

ለጥቃቱ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው አልሻባብ የሽብር ቡድን ‘አል አንዳለስ’ በተሰኘ ሬዲዮ ጣቢያ ላይ ሃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቆ፣ ታጣቂዎቼ 17 ሰዎችን ገድለዋል ብሏል።

ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሁለት የጤና ባለሞያዎች አንድ የተባበሩት አረብ ኤመሬት ከፍተኛ ባለስልጣን እና በድምሩ አራት ሰዎች መሞታቸውን ገልጸው ሌሎች ብዙዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።

የሶማሊያ ፕሬዘዳንት ሃሳን ሼኪ ሞሃመድ ሶና በተሰኘ መገናኝ ብዙሃን ላይ ቀርበው ለተባበሩት አረብ ኤመሬት ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG