በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ራፋን በምድር ለማጥቃት ዝግጅት ላይ ነች


ራፋ፣ ጋዛ ባለፈው መስከረም የተፈጸመውን ድብደባ (ፎቶ ፋይል ኤፒ 09/10/23)
ራፋ፣ ጋዛ ባለፈው መስከረም የተፈጸመውን ድብደባ (ፎቶ ፋይል ኤፒ 09/10/23)

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታንያሁ ሠራዊታቸው ከራፋ ሲቪሎችን እንዲያስወጣ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ፣ የአየር ኃይላቸው የጋዛ ሰርጥ ደቡባዊቷን ከተማ ዛሬ ደብድቧል። በምድር ለሚደረግ ጥቃት ዝግጅት ነው ተብሏል።

የአሶስዬትድ ፕረስ የዜና ወኪል የጤና ባለሥልጣናትን እና የዓይን ምስክሮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በአየር ጥቃቱ 28 ሰዎች ሲገደሉ፣ ከዚህ ውስጥ አስሩ ሕፃናት ናቸው ብሏል። በጥቃቱ በራፋ ከተማ አካባቢ በርካታ መኖሪያ ቤቶች እንደተመቱም ዜና አገልግሎቱ ዘግቧል።

“የምድር ወረራው እየመጣ ነው። በሰሜን እንዳደረጉት ሁሉ በራፋም ግድያ ሊቀጥሉ ነው። ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎች ተጨፍጭፈዋል። ዓለም ዝምታን መርጧል። ዓለም ጭፍጨፋ እንዲደረግ ፈቅዷል” ሲሉ የሰለባዎች አባት እንዲሁም አያት የሆኑት ፋዴል አል ጋናም ለዜና ወኪሉ ተናግረዋል።

አራት የሚሆኑ የሐማስ ሻለቃ ጦሮችን ለመደምሰስ በሚል፣ ከራፋ ሲቪሎች እንዲያስወጣ ለሠራዊቱ ትዕዛዝ መውረዱን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ትናንት ዓርብ አስታውቋል።

“በራፋ አራት የሐማስ ሻለቃ ጦር ተቀምጦ ሐማስን መደምሰስ አስቸጋሪ ነው። በሌላ በኩል ሲቪሎች በራፋ እያሉ ጠንካራ ሥራ መስራት አንችልም” ብለዋል ናታንያሁ ባወጡት መግለጫ።

1.4 ሚሊዮን የሚሆኑትና በራፋ የሚገኙትን ሲቪሎች የት ማስፈር እንደታቀደ መግለጫው ግልጽ አላደረገም ሲል አሶስዬትድ ፕረስ በዘገባው አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG