በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ኢራን እና ሩሲያ የአሜሪካን ጥቃት አወገዙ


ምስሉ የኢራቅ የሺዓ ህዝባዊ ንቅናቄ ሃይሎች አባላት የአሜሪካ የአየር ጥቃት በአልቃይም ከተፈፀመ በኋላ ፍርስራሽ ሲያጸዱ ይታያል።
ምስሉ የኢራቅ የሺዓ ህዝባዊ ንቅናቄ ሃይሎች አባላት የአሜሪካ የአየር ጥቃት በአልቃይም ከተፈፀመ በኋላ ፍርስራሽ ሲያጸዱ ይታያል።

ዩናይትድ ስቴትስ በሶሪያ እና ኢራቅ ውስጥ በሚገኙ ኢራንን ደጋፊ ታጣቂ ቡድኖች ላይ የወሰደቻቸው የአጸፋ ጥቃቶች ከሁለቱ አገራት ባለስልጣናት እና ሌሎች የደማስቆ እና ባግዳድ ወዳጅ ሀገራት ውግዘት ተከትሎታል ።

የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፋይሰል አል ሚቅዳድ ባስተላለፉት መግለጫ ላይ ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃት የቀጠናውን ውጥረት እንደሚያባብስ ተናግረዋል ። ። የሶሪያ መንግስት ቴሌቭዥን የሀገሪቱ የመከላካያ ሚኒስቴር ዩናይትድ ስቴትስ ያጠቃችው የእስላማዊ መንግስት ሽብርተኛ ቡድንን የሚዋጉትን የሶሪያ መንግስት ኃይሎችን መሆኑን እንዲሁም ሽብርተኞች ዳግም እንዲደራጁ ለማገዝ እየጣረች ነው በሚል መናገሩን ጠቅሷል ።

ራሚ አብዱል ራህማን የተባሉ እንግሊዝ ላይ መሰረቱን ያደረገው የሶሪያ ሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ ተቋም ባልደረባ በበኩላቸው ዩናይትድ ስቴትስ በኢራቅ ድንበር ላይ የሚገኘውን አል ቃየም ጣቢያን ጨምሮ ሀገሪቱን ከሶሪያ በሚያዋስነው ፣ በአል ቡካማል እና ዴር ኤል ዙር ስፍራዎች መካከል ጥቃት አድርሳለች ።

ራማን እንዳሉት ፣ ምንም እንኳን ከጥቃቱ ቀድሞ በተሰጠ ማንቂያ መልዕክት መሰረት አብዛኛውን ጊዜ ታጣቂዎች በዋሻዎች ውስጥ ቢሸሸጉም የኢራን አል ቃድ ኃይሎች ፣ የኢራን አብዩታዊ ዘብ ኃይሎች እንዲሁም አፍቃሪ ኢራን ሚሊሺያ ቡድኖች በዩናይትድ ስቴትስ ጥቃት ተመተዋል ።

በአልቃይም እና በአል ካሻት ከተማ በሚገኘው የኢራን ደጋፊ በሆኑት የሃሽድ አል ሻአቢ ሚሊሻዎች ዋና መሥሪያ ቤት በደረሰው የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃት ተጎጂ ለሆኑት ሰዎች ፣የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሺዓ አል-ሱዳኒ ይፋዊ የሃዘን ጊዜ አውጀዋል ።

የኢራቅ መንግስት ቃል አቀባይ እንዳሉት ቢያንስ 18 ሰዎች ተገድለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ያጠቃቻቸውን ሚሊሺያ ኃይሎች የምትደግፈው ኢራን ጥቃቱን " የሶሪያ እና ኢራቅን ሉዓላዊነት እና ግዛት ልዕልና የጣሰ" ስትል ጠርተዋለች ።የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ የዩኤስ አሜሪካን ጥቃት " የከፋ ስትራቴጂካዊ ስህተት" ብለውታል ።
የሶሪያ እና የኢራን አጋር የሆነችው ሩሲያ በበኩሏ ዩኤስ አሜሪካን “በመካከለኛው ምስራቅ ትርምስ እና ውድመት ትዘራለች” ስትል ከሳለች ።

የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤትን የጦር አገልግሎት ኮሚቴን የሚመሩት እንደራሴ ጃክ ሪድ ጠንካራ ቃላትን በኢራን ላይ የሰነዘሩ ሲሆን ፣ "በሶሪያ እና ኢራቅ የሚገኘው የኢራን የእጃዙር ጦር ከፍተኛ ምት ደርሶበታል ።በመካከለኛው ምስራቅ ዙሪያ የሚገኙ ከኢራን ጋር ትስስር ያላቸው ሚሊሻዎች በተመሳሳይ ተጠያቂ እንደሚሆኑ መረዳት አለባቸው" ብለዋል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG