የናሚቢያው ፕሬዚደንት ሀጌ ጋይንጎብ በ82 ዓመታቸው ዛሬ ማለዳ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ጽ/ቤት አስታወቋል። ጋይንጎብ ከሳምንታት በፊት የካንሰር ታማሚ መሆናቸው ተነግሮ ነበር።
ከፕሮስቴት ካንሰር እያገገሙ መሆናቸውን ይፋ ካደረጉበት የአውሮፓዊያኑ 2015 ዓመተ ምህረት ጀምሮ መጠነኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ያለባትን በእጅጉ ደረቃማ የሆነችውን ደቡብ አፍሪካዊት ሀገር አስተዳድረዋል።
ከፍተኛ የአልማዝ እንዲሁም የኤሌክትሪክ መኪና ግብዓት የሆነው ሊትየም ክምችት ያለባት የማዕድን መናገሻ ሀገር ናሚቢያ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ፕሬዚደንታዊ እና የፓርላማ ምርጫ እስክታካሂድ ምክትል ፐሬዚደንቱ ናንጎሎ ምቡማ እንደሚያስተዳድሯት ተነግሯል።
የፕሬዚደንት ጽህፈት ቤቱ ኤክስ በተሰኘው ገጽ ላይ የሞታቸውን ምክንያት ይፋ አላደረገም። ይሁንና ባለፈው ወር ፣ በመደበኛ ምርመራ የህመሙ ሁኔታ ከተለየ በኃላ ፣ ፕሬዚደንቱ ለሁለት ቀናት በካንሰር የተጠቁ ህዋሶች ህክምና ለማድረግ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ማምራታቸውን ተናግረው ነበር።
እ.ኤ.አ. በ1941 የተወለዱት ጋይንጎብ ናሚቢያ በ1990 ከአናሳ ነጮች አስተዳደር ስር ከነበረችው ደቡብ አፍሪካ ነፃነቷን ከማግኘቷ በፊት ጀምሮ ታዋቂ ፖለቲከኛ ነበሩ።
የናሚቢያን ሕገ መንግሥት ያረቀቀውን አካል በሊቀ መንበርነት መርተዋል፣ ከዚያም በዚያው ዓመት መጋቢት 21 ከነጻነት በኃላ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እስከ 2002 ድረስ ቆይተዋል።
በ2014 ዓም በሀገሪቱ የተካሄደውን ምርጫ 87 በመቶውን የመራጮች ድጋፍ በማግኘት ያሸነፉት ጋይንጎብ በ2019 በሀገሪቱ የተደረገውን ምርጫ ያሸነፉት ግን ከግማሽ በላይ የሆኑ መራጮችን በጠባቡ በተሻገረ ልዩነት ነው።
ምርጫውን ተከትሎ፣ ባለስልጣናት ሳመኸርጂ ለተሸነው የአይስላንድ ግዙፍ አሳ አጥማጅ ድርጅት ፣ ፍትሐዊ ያልሆነ የአሳ ምርት ኮታ አመቻችተዋል ፣ በምላሹም ጥቅም ሰብስበዋል የሚል መንግስታዊ ሙስናን የተመለከተ ውዝግብ ተቀስቅሷል ። የበረታው ቁጣ ሁለት ሚኒስትሮች ከስልጣናቸው እንዲለቁ አስገድዷል ።
ጌይንጎብ የናሚቢያ ሀብት በነጮች እጅ ውስጥ እንዲቆይ ባስተላለፉት ውሳኔም ይታወቃሉ ።መንግስታቸው በስራ ላይ ሊውል ያልቻለውን ነጮች የያዟቸው የንግድ ተቋማት 25 በመቶ ድርሻ ለጥቁር ናሚቢያውያን እንዲያስተላልፉ የሚያዘውን ፖሊሲ በሻሩ ማግስት በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የሀብት እና ታሪካዊ የዘር ልዩነት እንዳለ ያመኑት ጌይንጎብ ሀብትን ከነጮች ወስዶ ለጥቁሮች መስጠት ግን የማይሰምር ሀሳብ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጸዋል ።
ጌይንጎብ በህክምና ቡድናቸው ርዳታ እያገኙ በነበረበት በዊንድሆክ በሚገኘው ሌዲ ፖሃምባ ሆስፒታል ህይወታቸው ማለፉን የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት አስታውቋል።
መድረክ / ፎረም