በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ  ለአፍኮን ግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋገጡ 


ናይጄሪያ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ  ለአፍኮን ግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋገጡ 
ናይጄሪያ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ  ለአፍኮን ግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋገጡ 

በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (አፍኮን) የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ናይጄሪያ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት ለግማሽ ፍጻሜው ደረጃ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ትናንት አመሻሹን በፊሊክስ ሆፊየት ቦይግኒ ስታዲየም ቀድመው የተገናኙት የናይጄሪያ እና የአንጎላ ብሔራዊ ቡድኖች ነበሩ።


የጣልያኑ አታላንታ ቡድን የክንፍ ተጫዎች አዲሞላ ሉክማን በ41ኛው ደቂቃ በግራ መስመር ከሞሰስ ሳይመን የተሻገረለት ኳስ በግሩም ሁኔታ ከመረብ በማገናኘት የኃያል ንስሮችን ቡድን የድል ጉዞ አራዝሟል። ተደጋጋሚ ያልሰመሩ የግብ ሙከራዎችን ያከታተለው የአንጎላ ብሔራዊ ቡድን ከውድድር ውጭ ሆኗል ።

በመቀጠል በ"ኢቢምፒ" ስታዲየም የተገናኙት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ጊኒ ነበሩ ። የጊኒ ብሔራዊ ቡድን ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ዕድል ሞሃመድ ባዮ በ21ኛው ደቂቃ ከመረብ በማገናኘት የጨዋታውን ቀዳሚ ግብ ማስቆጠር ችሏል ። የጊኒ ደጋፊዎች የደስታ ቆይታ ግን ለ6 ደቂቂቃዎች ብቻ የዘለቀ ነበር ። በ27ኛው ደቂቃ የዲአር ኮንጎ ቡድን በቻንስል ቤምባ ማንጉሉ አማካኝነት አቻ የምታደርገውን ግብ አስቆጥሯል ። በ65ኛው ደቂቃ ያገኘውን የፍጸም ቅጣት ምት በዩሃን ዊሳ አማካይነት ወደ ጎል የቀየረው የዲአር ኮንጎ ቡድን አርዘር ማሳኩ በ82ኛው ደቂቃ ከርቀት በአስቆጠራት ግሩም ግብ ፣ በጊኒ መረብ ላይ በአጠቃላይ 3 ግቦችን በማዝነብ ጨዋታውን በድል አጠናቋል።

የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት የሚቀጥሉ ሲሆን ማሊ ከአዘጋጇ ሀገር ኮትዲዮቫር ፣ ኬፕ ቨርድ ከደቡብ አፍሪካ ይፋለማሉ ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG