በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ “ባፋና ባፋና”  ድል  እና “የአትላስ አንበሶች”  ሽኝት


የደቡብ አፍሪካ ቡድን የኦርላንዶ ፓይሬትስ ቡድን የፊት አጥቂ ኤቪደንስ ማክጎፓ ግብ የድል ግስጋሴውን የጀመረ ሲሆን ቲቦ ሞኮይና በ95ኛው ደቂቃ በቅጣት ምት ባስቆጠራት ድንቅ ሁለተኛ ግብ ድሉን የማይናጥ አድርጓል ።
የደቡብ አፍሪካ ቡድን የኦርላንዶ ፓይሬትስ ቡድን የፊት አጥቂ ኤቪደንስ ማክጎፓ ግብ የድል ግስጋሴውን የጀመረ ሲሆን ቲቦ ሞኮይና በ95ኛው ደቂቃ በቅጣት ምት ባስቆጠራት ድንቅ ሁለተኛ ግብ ድሉን የማይናጥ አድርጓል ።

የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን የሞሮኮ አቻውን ኮትዲዮቫር ፣ ሳንፔድሮ ላይ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ማለፉን አረጋግጧል።

በመልሶ ማጥቃት ላይ ያተኮረው በዙሉ ቋንቋ “ባፋና ባፋና ( ልጆቹ ፣ልጆቹ) በሚል ተቀጥያ መጠሪያው የሚታወቀው ቡድን በ57ኛው ደቂቃ በደቡብ አፍሪካ ፕሪሜር ዲቪሽን (የሀገር ውስጥ የክለቦች ፉክክር) ፣ለኦርላንዶ ፓይሬትስ ቡድን በሚጫወተው የፊት አጥቂ ኤቪደንስ ማክጎፓ ግብ የድል ግስጋሴውን የጀመረ ሲሆን ቲቦ ሞኮይና በ95ኛው ደቂቃ በቅጣት ምት ባስቆጠራት ድንቅ ሁለተኛ ግብ ድሉን የማይናጥ አድርጓል።

ካታር ላይ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ አራተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በአፍሪካ የእግር ኳስ ታሪክ አዲስ ልቅናን ያስመዘገበው የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ፍጹም ቅጣት ምትን ጨምሮ በርካታ የግብ ዕድሎችን ለፍሬ ሳያበቃ ቀርቷል። የቡድኑ የቀኝ ክንፍ ተጫዎች የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴን ጀርሜን ኮከብ አችራፍ አኪሚ የፍጹም ቅጣት ምት በመሳቱ ደጋፊዎቹን ለሀዘን እና ቁጭት የዳረገ ሲሆን ፣ ተከላካዩ ሶፊያን አምራቤት በደቡብ አፍሪካ ተጫዎች ላይ ጥፋት በመፈጸሙ ከጨዋታው በቀይ ካርድ ተሰናብቷል።

በዘንድሮው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ላይ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው “የአትላስ አንበሶች ” በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ከውድድሩ መሰናበቱ እርግጥ ሆኗል ። በአንጻሩ በቅርብ ጊዜያት አህጉራዊ ውድድሮች ተሳትፎው አመርቂ ውጤት ርቆት የነበረው የደቡብ አፍሪካ ቡድን በደማቅ ድሉ ለደጋፊዎቹ የማታ ደስታን አጎናጽፏል።ቡድኑ በመጭው ቅዳሜ ለሩብ ፍጻሜው ፉክክር ከኬፕ ቨርድ ብሔራዊ ቡድን ጋር ይጫወታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG