በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አማራ ክልል በመንፈቅ ዓመቱ የሰበሰበው ግብር የዕቅዱን ሩብ ብቻ እንደሆነ አስታወቀ


አማራ ክልል በመንፈቅ ዓመቱ የሰበሰበው ግብር የዕቅዱን ሩብ ብቻ እንደሆነ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:10 0:00

አማራ ክልል በመንፈቅ ዓመቱ የሰበሰበው ግብር የዕቅዱን ሩብ ብቻ እንደሆነ አስታወቀ

በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ምክንያት፣ በግማሽ ዓመቱ የተሰበሰበው ግብር ከታቀደው አንድ አራተኛ ብቻ እንደሆነ፣ የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።

በግማሽ ዓመቱ ከ71 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ቢታቀድም፣ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ እንዳልተቻለ፣ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ሓላፊ አቶ ፍቅረ ማርያም ደጀኔ አስረድተዋል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው ትላንት ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ በተለይም በምዕራባዊ ዞኖች ያለው የጸጥታ ችግር ለግብር አሰባሰቡ ዕንቅፋት እንደፈጠረ ገልጸዋል።

ግጭቱ በዚሁ ከቀጠለና ነጋዴውም በወቅቱ ግብር ካልከፈለ፣ መንግሥት ለሠራተኞች ደመወዝም የመክፈል አቅም ሊያጣ እንደሚችል አክለው አሳስበዋል፡፡

የክልሉ አንዳንድ ግብር ከፋዮች በበኩላቸው፣ ገቢዎች ቢሮን ጨምሮ በአካባቢያቸው የሚገኙ አንዳንድ የመንግሥት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ዝግ በመኾናቸው ነጋዴው የግብር ክፍያውን ሊፈጸም አለመቻሉን ተናግረዋል።

ዊል ኮንሰልት የተባለው የኢኮኖሚ የፋይናንስና የኢንቨስትመት የማማከር አገልግሎት ባለቤት እና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ይርጋ ተስፋዬ፣ መንግሥት ግብር ለመሰብሰብ አለመቻሉ፣ በክልሉ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ከማስከተሉም በላይ የተለመደ የግብር አሰባሰብ ሥርዓቱን ያዛባል፤ ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG