በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ ለተገደሉ ጋዜጠኞች፣ የደቡብ አፍሪካ የሙያ አጋሮች መታሰቢያ አደረጉ


ፋይል - የደቡብ አፍሪካ ፍትህ ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ሔግ በሚገኘው ፍርድቤት ፊት መግለጫ ሲሰጡ ጥር 11፣ 2024
ፋይል - የደቡብ አፍሪካ ፍትህ ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ሔግ በሚገኘው ፍርድቤት ፊት መግለጫ ሲሰጡ ጥር 11፣ 2024

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ በጋዛ ለተገደሉ የሙያ አጋሮቻቸው የመታሰቢያ ሻማ ማብራት ሥነ ስርዓት በጆሃንስበርግ ትናንት እሁድ አከናውነዋል።

ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ሲፒጄ እንደሚገምተው፣ በሐማስ እና በእስራኤል መካከል ጦርነት ከጀመረ ወዲህ፣ እስከ ትናንት እሁድ ድረስ 83 ጋዜጠኞች ተገድለዋል። ከእነዚህ ውስጥ 76 ፍልስጤማውያን፣ 4 እስራኤላውያን እና ሶስት ሌባኖሳውያን ይገኙበታል። በመታሰቢያው ሥነ ስርዓት ላይ የተናገሩት ጋዜጠኞች፣ ሙያው ገለልተኘትን በተመለከተ ስለገጠመው ፈተና አውስተዋል።

ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ 26ሺሕ83 ሰዎች እንድተገደሉ በጋዛ የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ከ64ሺሕ በላይ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል።

ደቡብ አፍሪካ እስራኤልን በዘር ማጥፋት ከሳ ሔግ በሚገኘው ፍርድ ቤት አቁማለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG