የአፍሪካ መሪዎች በሮም፣ ጣሊያን ከአገሪቱ ጠቃላይ ሚኒስትር ጋር ጉባኤ መቀመጣቸው ሲነገር፤ ጆርጂያ ሜሎኒ፣ ብዙ የተባለለትንና ለአህጉሪቱ የያዙትን የኃይል ዘርፍ እና ፍልሰትን የማስቆም ዕቅድ ይፋ ያደርጋሉ ተብሏል።
የቀኝ ዘመም መሪዋ ጆርጂያ መሎኒ፣ ከሁለት ዓመታት በፊት ወደ ሥልጣን የመጡት፣ በፀረ ፍልሰተኞች የምርጫ አጀንዳ ነበር።
የሜሎኒ ዕቅድ፣ በአፍሪካ እና በአውሮፓ መካከል የኃይል ድልድይ በመሆን፣ ለአውሮፓ ኃይል የሚቀርብበት፣ በአፍሪካ ደግሞ መዋዕለ ነዋይ የሚፈስበትን ዘዴ የቀየሰ ነው ተብሏል። ዕቅዱም በሙከራ ደረጃ በሚደረጉ ፕሮጀክቶች እንደሚጀመር ተገልጿል።
ኃይልን በተመለከተ አውሮፓ በሩሲያ ላይ ያላትን የነዳጅ ጥገኝነት ለመቀነስ ያለመ ነው ተብሏል።
የአውሮፓ ኅብረት በበኩሉ ለአፍሪካ 160 ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል የተባለ ዕቅድ በተመሳሳይ በመያዙ፣ የጣሊያን ዕቅድ ድጋፍ ሊያጥረው ይችላል ተብሏል።
በተጨማሪም ዕቅዱ አፍሪካ በምታገኘው የኃይል መዋዕለ ነዋይ ምትክ፣ ፍልሰትን መግታት እንደሚጠበቅባት ተመልክቷል።
መድረክ / ፎረም