በታጠቁ ሶማሊያዊ የባሕር ላይ ጠላፊዎች ታግታ ነበር የተባለችን የስሪላንካ መርከብ የሲሼልስ ኃይሎች ማስለቀቃቸውን የአገሪቱ ፕሬዝደንት ቢሮ አስታውቋል።
የሲሼልስ ልዩ ወታደራዊ ኃይል መርከቧን መቆጣጠሩና በውስጡ የነበሩ ስሪላንካውያንን ማዳኑን የፕሬዝደንቱ ቢሮ ጨምሮ ገልጿል።
‘ሎሬንዞ ፑታ - 4’ የተባለቸው መርከብ፣ ከሶማሊያ መዲና ሞቃዲሹ 840 ማይል ርቀት ላይ ተይዛ እንደነበር የስሪላንካ ባሕር ላይ አስታውቋል።
መርከቧ ወደ መዲናዋ ቪክቶሪያ በማቅናት ላይ መሆኗም ታውቋል።
የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት መፈንዳቱን ተከትሎ፣ በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማፂያን በቀይ ባሕር ላይ በሚተላለፉ መርከቦች ላይ ጥቃት በመሠንዘር ላይ በመሆናቸውና በዚህም ምክንያት በየመን ባሕረ ሠላጤ የነበሩ ዓለም አቀፍ የባሕር ኃይሎች ወደ ቀይ ባሕር በመዝለቃቸው፣ በሶማሊያ የሚገኙ የባሕር ላይ ጠላፊዎች እንደገና እንዳያንሰራሩ ተሰግቷል።
ባለፈው ሕዳር፣ አንድ የቡልጋሪያ ጅምላ ጫኝ መርከብ በሶማሊያዊ የባሕር ላይ ጠላፊዎች መታገዷ ሲታወቅ፣ ክስተቱ ከስድስት ዓመታት ወዲህ የተፈጸመ ስኬታማ የሆነ ጠለፋ ነው ተብሏል።
መድረክ / ፎረም