በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለፍልስጤማውያን የርዳታ ድርጅት ድጋፍ ያቋረጡ አገራት ውሳኔያቸውን እንደገና እንዲያጤኑ ተጠየቀ


ፍልስጤማውያን በጋዛ እርዳታ በማስተባበርና በማሰራጭት ከፍተኛ ሥራ የሚሠራው የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲ (UNRWA) የሚያደርሰውን ዱቄት ሲቀበሉ - ጥር 29፣ 2024
ፍልስጤማውያን በጋዛ እርዳታ በማስተባበርና በማሰራጭት ከፍተኛ ሥራ የሚሠራው የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲ (UNRWA) የሚያደርሰውን ዱቄት ሲቀበሉ - ጥር 29፣ 2024

አገራት በተመድ ስር ለሚተዳደረው የፍልስጤማውያን የርዳታ ድርጅት ይሰጡት የነበረውንና ለጊዜው ለማቋረጥ የወሰኑትን ድጋፍ እንደገና እንዲያጤኑ የተመድ ባለሥልጣናት ጠይቀዋል።

በፍልስጤማውያኑ የርዳታ ድርጅት ውስጥ ከሚሠሩት 13ሺሕ ሠራተኞች ውስጥ፣ በደርዘን የሚቆጠሩት፣ “ሐማስ ጥቃት በፈፀመበት ወቅት ተሳትፈዋል” ስትል እስራኤል ክስ ማሰማቷን ተከትሎ፣ ዋና ለጋሾቹን አሜሪካና ጀርመንን ጨምሮ ቢያንስ ዘጠኝ አገራት የገንዘብ ርዳታቸውን አቋርጠዋል።

የተመድ ዋና ፀሓፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ትናንት እሁድ ባደረጉት ጥሪ፣ “ርዳታቸውን ያቋረጡት መንግስታት የፍልስጤማውያኑ ርዳታ ድርጅት ሥራዎችን መቀጠል እንዲችል እንዲያድርጉ ጠይቀዋል።”

በሽብር ሥራ ተሰማርተዋል የተባሉት የተመድ ሠራተኞችንም ተጠያቂ እንደሚያደርጉ ጉቴሬዥ ቃል ገብተዋል። 12 ሠራተኞች ተጠያቂ የተደረጉ ሲሆን፣ ዘጠኙ ከድርጅቱ መባረራቸውንም ዋና ፀሓፊው አስታውቀዋል። የወንጀል ክስ ሊከተል እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል። በተለምዶ የተመድ ሠራተኞች ከሥራቸው ጋር በተያያዘ ለሚፈፀሙ ነገሮች ተጠያቂ አይሆኑም።

እስራኤል ያቀረበችውን ክስ ተመድ በመመርመር ላይ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG