በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ እና አንጎላ ለሩብ ፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋገጡ


"ኃያል ንስሮች" አዲሞላ ሉክማን አከታትሎ ባስቆጠራቸው 2 ግቦች የረጅም ጊዜ ተቀናቃኛቸው የካሜሮን ብሔራዊ ቡድንን ድል አድርገዋል።
"ኃያል ንስሮች" አዲሞላ ሉክማን አከታትሎ ባስቆጠራቸው 2 ግቦች የረጅም ጊዜ ተቀናቃኛቸው የካሜሮን ብሔራዊ ቡድንን ድል አድርገዋል።

ኮትዲዮቫር አዘጋጅነት በመከናወን ላይ ያለው የአፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች በትናንትናው ዕለት ተጀምረዋል። በትናንትናው ዕለት በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ደቡብ ምዕራብ አፍሪካዊት ሀገር አንጎላ እና ምዕራብ አፍሪካዊቷ ናይጄሪያ ተፎካካሪዎቻቸውን በመርታት ለሩብ ፍጻሜ ምዕራፍ ተሸጋግረዋል። አንጎላ ጎረቤት ሀገር ናሚቢያን 3 ለ 0 በረታችበት ጨዋታ ጊልሰን ዳላ 2 ግቦችን ሲያስቆጥር ማቡሉሉ 1 ግብ አክሏል። በዚህ ጨዋታ 2 ተጫዎቾች የቀይ ካርድ ሰለባ መሆናቸውን ተከትሎ ሁለቱም ቡድኖች በ10 ተጫዎቾች የተመደበውን ሰዓት አጠናቀዋል።

በፊሊክስ ሆፕዌ ቦይግኒ ስታዲየም በተደረገው ሁለተኛ ጨዋታ ላይ የተገናኙት በአህጉሩ የእግር ኳስ ታሪክ የላቀ ስም ያላቸው ናይጄሪያ እና ካሜሩን ነበሩ። "ኃያል ንስሮች" አዲሞላ ሉክማን አከታትሎ ባስቆጠራቸው 2 ግቦች የረጅም ጊዜ ተቀናቃኛቸው የካሜሮን ብሔራዊ ቡድንን ድል አድርገዋል። "የማይበገሩ አናብስት " በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የካሜሮን ብሄራዊ ቡድን በዘንድሮ አቋሙ ትችት ሲቀርብበት የነበረው ሲሆን ፣ ከትናንቱ ሽንፈት በኃላ ከውድድሩ መሰናበቱ ርግጥ ሆኗል ።የናይጄሪያ እና የአንጎላ ብሔራዊ ቡድኖች ለግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ የፊታችን አርብ ይፋለማሉ።

ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በኃላ ወደ ሩብ ፍጻሜ የሚልፉ ቡድኖችን ለመለየት ተጨማሪ ጨዋታዎች ይከናወናሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዘንድሮ የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ላይ ድንቅ ብቃታቸውን ካሳዩ ያልተጠበቁ ቡድኖች መካከል ዘንዱ የሆነው የሆነው የኢኳቶሪያል ጊኒ ብሔራዊ ቡድን እና የጊኒ አቻው በአላሰን ዋታራ ስታዲየም ይገናኛሉ። ከዚህ ጨዋታ በመቀጠል የግብጽ ብሔራዊ ቡድን ከዲ.አር ኮንጎ ቡድን ጋር የጋለ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ።ጨዋታው የሚከናወነው በሳን ፔድሮ ከተማ በሚገኘው ሎሪየንት ፖኩ ስታዲየም ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG