በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምዕራባዊያን ሀገራት ለጋዛ የሚያደርጉትን ድጋፍ ሊያቋርጡ ነው


ጋዛ ጥር 2016
ጋዛ ጥር 2016

የመንግስታቱ ድርጅት የፍልስጤም ተራድዖ ድርጅት አባላት በጥቅምት ሰባቱ የሀማስ ጥቃት ላይ ተሳታፊ ነበሩ የሚለው ክስ ከተሰማ በኋላ፤ ድጋፋቸውን መጨረሻ ላይ ካቋረጡ ሀገራት መካከል ጣሊያን አንዷ ናት። አውስትሬሊያ፣ ካናዳ እና ዩናይትድ ስቴትስም ለጋዛ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲሚያቋርጡ ካስታወቁ ሀገራት መካከል ናቸው።

በሀማስ ስር የሚተዳደረው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ትላንት ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ 174 ፍልስጤማዊያን መገደላቸውን እና 310 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቋል። በጎሮጎሳዊያኑ ጥቅምት ወር ላይ ሀማስ ካፈጸመው ጥቃት በኋላ እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ 26,257 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 64,797 የሚሆኑ ሰዎች መጎዳታቸውን ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ጨምሮ አስታውቋል።

የፍልስጤም ነጻነት ተቋም ዋና ስራ አስፈጻሚ ሁሴን አል ሼኪ ለተ.መ.ድ ተራድዖ ተቋም ድጋፋቸውን ያቋረጡ ተቋማት ፍልጤማዊያን ያሉበትን ሁኔታ እንዲያጤኑ ተመጽነዋል።

በሌላ በኩል ትላንት አርብ ዋይት ሀውስ በሀማስ የታገቱ እስራኤላዊያንን መለቀቅን በተመለከተ ድርድሮች ሊኖሩ ይችላሉ ሲል ጠቁሟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG