በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእሥራኤል ላይ የቀረበው የዘር ማጥፋት ክስ ውድቅ እንደማይደረግ የመንግሥታቱ ድርጅት አስታወቀ


የዓለም አቀፉ የፍትሕ ችሎት ፕሬዚዳንት ጆአን ኢ ዶኖጉ
የዓለም አቀፉ የፍትሕ ችሎት ፕሬዚዳንት ጆአን ኢ ዶኖጉ

የተባበሩት መንግሥታት የወንጀል ችሎት እሥራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ተከትሎ የቀረበባትን የዘር ማጥፋት ክስ ውድቅ ላለማድረግ መወሰኑን ዛሬ አስታወቀ።

ዓለም አቀፉ የፍትሕ ችሎት ፕሬዚዳንት ጆአን ኢ ዶኖጉ፣ የችሎቱን ውሎ የከፈቱት፣ 17 አባላት ያሉት የዳኞች ቡድን የጋዛውን ግጭት አስመልክቶ የደረሰበትን እና ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን በእጅጉ ሲጠበቅ የቆየ ውሳኔ በንባብ በማሰማት ነው።

"ችሎቱ በአካባቢው እየተፈጸመ ያለውን አሳዛኝ ሰብአዊ ጉዳት ጠንቅቆ ያውቃል። በሰው ልጆች ላይ የሚደርስ ማብቂያ ያልተበጀለት ውድመት እና ስቃይ ችሎቱን በጥልቅ ያሳስበዋል" ሲሉም አክለዋል።

ችሎቱ በአካባቢው እየተፈጸመ ያለውን አሳዛኝ ሰብአዊ ጉዳት ጠንቅቆ ያውቃል። በሰው ልጆች ላይ የሚደርስ ማብቂያ ያልተበጀለት ውድመት እና ስቃይ ችሎቱን በጥልቅ ያሳስበዋል"

እስራኤል በበኩሏ የቀረበበትን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመቃወም ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ክሱን ውድቅ እንዲያደርግ ጠይቃ ነበር።

የዛሬው የችሎቱ ውሳኔ ጊዜያዊ ሲሆን፣ ደቡብ አፍሪካ ያቀረበችው ይህ ክስ በውል ተመርምሮ አንዳች ብይን እስኪሰጥ ድረስ ግን ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል ይታመናል። ፍርድ ቤቱ በደምቡ መሰረት ጉዳዩን እያየ ባለበት በአሁኑ ወቅት "እጅግ አጣዳፊነቱን" ከግምት በማስገባት በጋዛ በፍልስጤማውያን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ለመታደግ ጊዜያዊ ገደብ የሚጥሉ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ዳኞቹን ጠይቃለች።

ደቡብ አፍሪካ ካቀረበቻቸው ዝርዝር ጥያቄዎች ውስጥ ቀዳሚው እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ “በአስቸኳይ እንድታቆም" ችሎቱ እንዲያዝ የሚለው ሲሆን፤ እስራኤል በተጨማሪም የዘር ማጥፋትን ለመከላከል የሚያስችሉ እና በእጅጉ አስፈላጊ የሆነው የሰብአዊ እርዳታ ለተረጂዎች የሚተላለፍበትን መንገድ በመፍቀድ "ሚዛናዊ” ያለቻችውን እርምጃዎች እንድትወስድ የሚለው ይገኝበታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG