በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብፅና ኢትዮጵያ እየተካሰሱ ነው


ግብፅና ኢትዮጵያ እየተካሰሱ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

የግብፅ መግለጫዎች “ኢትዮጵያን አያሸብሩም” ሲሉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ግብፅን ኢትዮጵያን በማወክ ዘመቻ የከሰሱት አምባሳደር መለስ ሃገራቸው ከሶማሊላንድ ጋር የገባችው መግባባት ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲያገኝ በመጣር እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።

የግብፅ ፕሬዚዳንት “ሶማሊያን ማንም እንዲያስፈራራ አንፈቅድም” ሲሉ ሰሞኑን ለወረወሩት መልዕክት ሲመልሱ “ለሶማሊያ ግብፅ ከኢትዮጵያ በላይ አሳቢ ልትሆን አትችልም” ብለዋል። በቅርቡም ካይሮ ላይ በተካሄደ የአረብ ሊግ የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ “ኢትዮጵያ በአካባቢው ያለመረጋጋት ምንጭ ሆናለች” ሲሉ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ ተናግረው ነበር።

XS
SM
MD
LG