በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሸገር ከተማ የታሰሩ የሃይማኖት አባቶች የዐሥር ቀን ቀጠሮ ተጠየቀባቸው


“የመንበር ምሥረታ” ያሉትን እንቅስቃሴ ከሚያስተባብሩት አንዱ እንደሆኑ የጠቀሱት ዲያቆን አክሊሉ ዓለሙ
“የመንበር ምሥረታ” ያሉትን እንቅስቃሴ ከሚያስተባብሩት አንዱ እንደሆኑ የጠቀሱት ዲያቆን አክሊሉ ዓለሙ

በ“መንበረ ጴጥሮስ” ስም የሚጠራ “የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መሥርተናል” በሚል መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ የታሰሩት የሃይማኖት አባቶች፣ ዛሬ ፍርድ ቤት እንደቀረቡና የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንደተጠየቀባቸው ጠበቃቸው ተናገሩ፡፡

ከእንቅስቃሴው ጋራ በተያያዘ የታሰሩት የሃይማኖት አባቶች እና አገልጋዮች ቁጥር ዘጠኝ መድረሱንም፣ ከ“መንበረ ጴጥሮስ” ምሥረታ አስተባባሪዎቹ አንዱ እንደኾኑ የጠቀሱት ዲያቆን አክሊሉ ዓለሙ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

የእስር ርምጃውን አስመልክቶ፣ ከሸገር ከተማ አስተዳደር እና ከፖሊስ መምሪያው ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬም አልተሳካም።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በኩልም፣ እስከ አኹን ጉዳዩን አስመልክቶ የወጣ ይፋዊ መግለጫ የለም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

በሸገር ከተማ የታሰሩ የሃይማኖት አባቶች የዐሥር ቀን ቀጠሮ ተጠየቀባቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG