በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን ለጦርነት እየተዘጋጁ ነው” - ላቭሮቭ


የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ
የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ

“አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን ከሰሜን ኮሪያ ጋር ጦርነት ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው” ሲሉ የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ትናንት ረቡዕ ክስ አሰምተዋል።

ሶስቱ አገራት በበኩላቸው፤ በጋራ የሚያደርጉት ወታደራዊ ልምምድ በመከላከል ላይ ያተኮረ እና ከሰሜን ኮሪያ በመምጣት ላይ ያለውን የኑክሌር ስጋት ለመቋቋም ያለመ መሆኑን ይናገራሉ።

በተመድ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት ላቭሮቭ፤ ከደቡብ ኮሪያ የሚሰማው ትርክት፣ ድንገት ሰሜን ኮሪያ ላይ አነጣጥሯል ብለዋል።

በተመሳሳይ ከጃፓን የሚሰማው መልዕክትም "ተንኳሽ" እንደሆነ ላቭሮቭ አመልክተዋል።

“የወታደራዊ ትብብሩ ዓላማ፣ ከኮሪያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር ለውጊያ መዘጋጀት እንደሆነ ግልጽ ሆኗል” ብልዋል ላቭሮቭ።

ሶስቱ አገራት፣ የአሜሪካንን አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ያሳተፈ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ፣ ባለፈው ሳምንት አድርገዋል።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጁንግ ኡን በበኩላቸው፣ ተከታታይ የሚሳዬል ሙከራዎችን በማድረግ ላይ ናቸው።

ሩሲያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላት ግንኙነት በጥሩ ሁኔታ እያደገ መሆኑን ላቭሮቭ ጠቁመዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG