በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በኒው ሃምፕሸር ድል ወደ ሪፐብሊካን ፓርቲው እጩነት ተጠግተዋል


የሪፐብሊካን ፓርቲው ፕሬዚደንታዊ እጩ ለመሆን የሚወዳደሩት የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በኒው ሃምፕሸር
እአአ ጥር 23/2024
የሪፐብሊካን ፓርቲው ፕሬዚደንታዊ እጩ ለመሆን የሚወዳደሩት የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በኒው ሃምፕሸር እአአ ጥር 23/2024

የሪፐብሊካን ፓርቲው ፕሬዚደንታዊ እጩ ለመሆን የሚወዳደሩት የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በትናንቱ የኒው ሃምፕሸር ክፍለ ግዛት ቅድመ ምርጫ ከ54 ከመቶ በላይ ድምጽ በማግኘት ከፍተኛ ድል ተቀዳጅተዋል፡፡

ትረምፕ በኒው ሃምፕሸር ፕሬዝዳንታዊ የቅድመ ምርጫ ፉክክሮች ለሶስተኛ ጊዜ በማሸነፍ ታሪክ ሠርተዋል፡፡

በኒው ሃምፕሸር ያስመዘገቡት ስኬት የፓርቲዎቹ አባላት እጩ ለመምረጥ ውይይት የሚያደርጉበትና ድምጽ በሚሰጡበት በአዮዋ (ኮከስ) ያገኙትን የ30 ነጥብ ብልጫ ተከትሎ፣ በ40 ዓመታት ውስጥ ሁለቱንም ቅድመ ምርጫ ውድድሮች በድል የጨረሱ የመጀመሪያ ስልጣን ላይ ያልሆኑ የሪፐብሊካን ፓርቲ ተፎካካሪ ያደርጋቸዋል፡፡

ለዚህ የትረምፕ ድል ባለፈው እሁድ ራሳቸውን ከምርጫው አግልለው ድጋፋቸውን ለትረምፕ የቸሩት የፍሎሪዳው ገዥ ሮን ደሳንቲስ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተመልክቷል፡፡

14 የሪፐብሊካን ፓርቲው እጩ ተፎካካሪዎች በየተራ ከፉክክሩ የወጡ ሲሆን የቀሩት ብቸኛ የትረምፕ ተፎካካሪ የቀድሞዋ የተባበሩት መንግስታት አምባሳደር ኒኪ ሄሊ ኒው ሃምሸር ላይ 43 ከመቶ ድምጽ በማግኝታቸው ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል፡፡

ትረምፕ እና ሄሊ በመቀጠል በመጭው የካቲት ደቡብ ካሮላይና በሚካሄደው ቅድመ ምርጫ ይፎካከራሉ።

ሄሊ የቀድሞ የግዛቱ አገር ገዥ የነበሩ ሲሆን፣ ትራምፕም ከክልሉ ባለስልጣናት ድጋፍ ሲያሰባስቡ ቆይተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG