በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በደማስቆ ባካሄደችው ጥቃት ከፍተኛ የኢራን አዛዦችን ገደለች


ነፍስ አድን ሰራተኞች፣ በደቡባዊ የሊባኖስ ክፍል በሚገኝ ከተማ ውስጥ የእስራኤል ድሮን ባደረሰው ጥቃት የወደመውን መኪና ሲያነሱ - ጥር 20፣ 2024
ነፍስ አድን ሰራተኞች፣ በደቡባዊ የሊባኖስ ክፍል በሚገኝ ከተማ ውስጥ የእስራኤል ድሮን ባደረሰው ጥቃት የወደመውን መኪና ሲያነሱ - ጥር 20፣ 2024

እስራኤል ቅዳሜ እለት፣ በሶሪያ ዋና ከተማ፣ ደማስቆ፣ በሚገኝ የኢራን ወታደራዊ ኢላማ ላይ ባደረሰችው ጥቃት፣ ቢያንስ አምስት የታህራን አል ቃድ ኃይሎች አምስት ዋና አዛዦች መገደላቸው ተገለጸ።

ጥቃቱ አንድ የመኖሪያ ህንፃን ሙሉ ለሙሉ ያወደመ ሲሆን፣ ጥቃት የደረሰባቸው ሙሉ ለሙሉ ፍርስራሹ ውስጥ ተቀብረዋል። የሶሪያ ቴሌቭዥንም፣ አንድ ክሬን ከፍርስራሹ ስር ያሉትን አስክሬኖች ለማውጣት ሲሞክር አሳይቷል።

እስራኤል በይፋ ጥቃቱን ማካሄዷን ባትገልፀም፣ መቀመጫውን በለንደን ያደረገ የሶሪያ ሰብዓዊ መብት ተቋም ውስጥ የሚያገለግሉት ራሚ አብዱል ራህማን፣ እስራኤል ህንፃውን በሮኬት እንደመታች እና እንዳወደመች እንደሚያምኑ ለአረብ ሚዲያዎች ተናግረዋል።

ጥቃት የደረሰበት አካባቢም የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ እንዲሁም፣ የእስላማዊው ጂሃድ ድርጅት እና የሊባኖሱ ሂዝቦላ ሚሊሺያ ኃይሎች የሚገኙበት እንደሆነም ተናግረዋል።

በተጨማሪም የእስራኤል ንብረት የሆነ ሰው አልባ አይሮፕላን (ድሮን) ቅዳሜ ከሰዓት በኃላ በደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ፣ ሁለት የሂዝቦላ አዛዦች በተሳፈሩበት ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ማድረሱን አንድ የአረብ ሚዲያ ዘግቧል። ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ማንነታቸውን ለማረጋገጥ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውም ተዘግቧል።

ዩናይትድ ስቴትስ በሚገነው ኦክላሃማ ዩንቨርስቲ የመካከለኛው ምስራቅ ጥናት ፕሮግራም የሚመሩት ጆሽዋ ላንዲስ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ እስራኤል እና ኢራን ዩናይትድ ስቴትስን ወደ ትልቅ ቀጠናዊ ግጭት ለመሳብ እየሞከሩ ነው ብለዋል።

ከቅርብ ቀናት ወዲህ የኢራን ደጋፊ ሚሊሺያ ተዋጊዎች፣ በኢራቅ እና በሶሪያ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮችን ኢላማ እያደረጉ ሲሆን፣ ኢራን፣ የየመን ሁቲዎች በቀይ ባህር ላይ የሚገኙ የአሜሪካ መርከቦችን ኢላማ በማድረግ አሜሪካ ወደ ሰፊው ቀጠናዊ ግጭት እንድትሳብ አድርጋለች ሲሉ ላንዲስ አመልክተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG