በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በድጋሚ የተመረጡት የኮንጎ ፕሬዝዳንት ሺሴኬዲ ቃለ መሃላ ፈፀሙ


A Constitutional Court judge hands the national flag to President Felix Tshisekedi after taking the oath of office, on the day of his ceremony at the Stade des Martyrs in Kinshasa, on January 20, 2024.
A Constitutional Court judge hands the national flag to President Felix Tshisekedi after taking the oath of office, on the day of his ceremony at the Stade des Martyrs in Kinshasa, on January 20, 2024.


በታህሳስ ወር የተካሄደውን አወዛጋቢ ምርጫ አሸንፈው ትላንት ቃለ መሃላ ይፈፀሙት የኮንጎ ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ሺሴኬዲ፣ በሁለተኛው የአምስት ዓመት ስልጣን ዘመናቸው መካከለኛው አፍሪካን አንድ ለማድረግ እና ግጭት በሚካሄድበት ምስራቃዊው የሀገሪቱ ክፍል የሚኖሩ ንፁሃንን ህይወት ለመጠበቅ ቃል ገብተዋል።


በርካታ የሀገር መሪዎች በተገኙበት ቃለ መሃላቸውን ያካሄዱት የ60 ዓመቱ ሺሴኬዲ፣ "በእኔ ላይ እምነት ጥላችሁ የሰጣችሁኝን የመሪነት ኃላፊነት ተቀብያለሁ። የበለጠ የተዋሃደ፣ ጠንካራ እና የበለፀገ ኮንጎ እንፈልጋለን።" ብለዋል።


ሺሴኬዲ እ.አ.አ በ2019 ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡት፣ ኮንጎ እ.አ.አ በ1960 ከቤልጂየም ነፃ ከወጣች በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደችው ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ነው። ሺሴኬዲ ለሁለተኛ ጊዜ የተመረጡት 70 ከመቶ በላይ የሆነ ድምጽ በማግነት አሸንፈው መሆኑን የሀገሪቱ ብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል። ይሁን እንጂ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች እና ደጋፊዎቻቸው በርካታ ችግሮች የነበሩበት ምርጫ ተዓማኒነት የለውም ሲሉ ጥያቄ አንስተው ነበር።

የተቃዋሚ ተፎካካሪዎች ደጋፊዎቻቸው የፕሬዝዳንቱን ቃለ መሃላ ተቃውመው እንዲወጡ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም፣ ቅዳሜ እለት ግን ምንም አይነት የተቃውሞ ሰልፍ ሳይካሄድ ቀርቷል።

ለሁለት አስርት አመታት በሀገሪቱ ተሰማርቶ የነበረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ቡድን ተልዕኮውን ጨርሶ እየወጣ ነው። የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ሃይል ወታደሮችም እየወጡ ነው። በመሆኑም ፣ የፖለቲካ ተንታኞች በምስራቅ ኮንጎ ያለው ሰላም እና መረጋጋት ከአገሪቱ አንገብጋቢ ጉዳዮች አንዱ መሆኑን ይገልፃሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG