በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ እስራኤልን  በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማዊያንን በማሰር እና በማንገላታት ወንጀል  ከሰሰ


ከእስር የተለቀቁት ግለሰቦች ለረዥም ጊዜያት ዐይኖቻቸው በጨርቅ ተሸፍነው እንደነበረ እና ቦታውን በውል ባያውቁትም ወደ እስራኤል መወሰዳቸውን መናገራቸውን ወኪሉ ተናግረዋል ።
ከእስር የተለቀቁት ግለሰቦች ለረዥም ጊዜያት ዐይኖቻቸው በጨርቅ ተሸፍነው እንደነበረ እና ቦታውን በውል ባያውቁትም ወደ እስራኤል መወሰዳቸውን መናገራቸውን ወኪሉ ተናግረዋል ።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ እስራኤል በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያንን በጋዛ እና በዌስት ባንክ ሚስጥራዊ ቦታዎች አስራ እንደ ማሰቃየት የሚቆጠር እንግልት አድርሳባቸዋለች ሲል በትናንትናው ዕለት ከሷል።
በእስራኤል ቁጥጥር ስር በሚገኘው የፍልስጤም ግዛት የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ ተወካይ አጂት ሰንግሃይ በጄኔቫ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በእስራኤል መከላከያ ሃይል ከ30 እስከ 55 ቀናት ለሚደርስ ጊዜ ተይዘው እንደነበር የሚናገሩ “በርካታ” ሰዎችን እንዳገኙ ተናግረዋል።


ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም ታሳሪዎች በሺዎች እንደሚቆጠሩ መስማታቸውን ሰንግሃይ አክለዋል ። እንደ ማሳቀየት ተግባራት የሚቆጠር ድብደባ፣ ማዋረድ እና እንግልት እንደረሰባቸው መናገራቸውም ተጠቅሷል ። አንዳንድ ወንዶች በቀዝቀዛ የአየር ሁኔታ ውስጥ ካለ በቂ አልባስ በእራፊ ጨርቅ ብቻ ስለ መለቀቃቸው የሚናገሩ ዘገባዎች እንዳሉም ተወካዩ አክለዋል ። ከእስር የተለቀቁት ግለሰቦች ለረዥም ጊዜያት ዐይኖቻቸው በጨርቅ ተሸፍነው እንደነበረ እና ቦታውን በውል ባያውቁትም ወደ እስራኤል መወሰዳቸውን መናገራቸውን ወኪሉ ተናግረዋል ።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ ቃል አቀባይ ራቪና ሳምሳዲኒ በበኩላቸው ፣ ተፈጽሟል የተባለውን በደል በተመለከተ የእስራኤል ባለስልጣናትን ለማግኘት እንደጣሩ ሆኖም ምንም ዐይነት ምላሽ እንዳላገኙ ተናግረዋል ።በጄኔቫ የሚገኘውን የእስራኤል ልዑክ ቪኦኤ ለማግኘት ሞክሮ በተመሳሳይ መልስ ሳያገኝ ቀርቷል ።

ታጣቂው ቡድን ሃማስ በደቡባዊ እስራኤል በአውሮፓዊያኑ ጥቅምት 7 ቀን ባደረሰው ጥቃት በብዛት እስራኤላዊ የሆኑ 1,200 ሲገድል ወደ 250 ሰዎች አግቶ ወስዷል። ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት የእስራኤላውያን ኃይሎች ከባድ ምላሽ ተከትሎታል ። ሃማስ በሚመራው የጋዛ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቆጠራ መሠረት ከ 24,000 በላይ ሰዎች በእስራኤል የመልስ ጥቃት ተገድለዋል ፣ ከእነዚህ መካከል 70% ሴቶች እና ሕፃናት ናቸው ።ከዚህ በተጨማሪ ቢያንስ ሌሎች 60,000 መቁሰላቸውም ተነግሯል ።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ እስራኤል ሁሉም በቁጥጥር ስር የሚገኙም ሆነ ለእስር የተዳረጉ ሰዎች በዓለም አቀፍ የሰብአዊ ህግ ልማድ እና ደረጃዎች መሰረት መያዛቸውን እንዲሁም ደርሰዋል በተባሉ በደሎች ዙሪያ ምርመራ መደረጉን እስራኤል ማረጋገጥ አለባት ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG