በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያ 5 እህትማማቾች መታፈናቸው ህዝባዊ ቁጣን ቀስቅሷል


በወንጀለኛ ቡድኖች የተደጋገመው ለገንዘብ ብሎ ሰዎችን ማፈን በናይጄሪያ ዋነኛ ችግር ሆኖ ቆይቷል ።
በወንጀለኛ ቡድኖች የተደጋገመው ለገንዘብ ብሎ ሰዎችን ማፈን በናይጄሪያ ዋነኛ ችግር ሆኖ ቆይቷል ።

በናይጄሪያ አቡጃ ከተማ አቅራቢያ አምስት እህትማማቾች ታፍነው መወሰዳቸው በመላ ሀገሪቱ ቁጣ መቀስቀሱን ተከትሎ ፣ በሀገሪቱ ዋና ከተማ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ስጋት ፈጥሯል።

እህትማማቾች የታፈኑት በአውሮፓዊያኑ ዓመት መጀመሪያ ላይ ከአቡጃ እምብርት 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸውን ጥሰው በገቡ የታጠቁ ሰዎች መሆኑን አንድ የቤተሰብ አባል ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግራለች ።


የተጠየቀው ማስፈቻ ገንዘብ በቀነ -ገደቡ አለመከፈሉን ተከትሎ ፣ጥቃት አድራሾቹ ከእህትማማቾቹ መካከል አንዷ የሆነችው የ21 ዓመቷ ናቢሃ አልካድርሪያን እንደገደሉ ተናግራለች። ሌሎቹን ለማስፈታት ድርድር ቀጥሏል።

በወንጀለኛ ቡድኖች የተደጋገመው ለገንዘብ ብሎ ሰዎችን ማፈን በናይጄሪያ ዋነኛ ችግር ሆኖ ቆይቷል ። ወንጀለኛ ቡድኖቹ ተማሪዎችን ከትምህርት ቤቶች ውሰጥ ሳይቀር ያፍናሉ ።የእህትማማቾች መታፈን የቀሰቀሰውን የህዝብ ቁጣ ተከትሎ ፣ ፕሬዚደንት ቦላ አህመድ ቲኑቡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተንሰራፍቷል ያሏቸውን የአፈና እና የሽፍትነት ጥቃቶች አውግዘዋል ።


ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግለት የፌዴራል ዋና ከተማ ግዛት ውስጥ የወንጀል ቡድኖች ጥቃት ማድረሳቸው ከታወቀ ወዲህ ፖለቲከኞች እና ብዙሃን መገናኛዎች የመንግስትን ስትራቴጂ ጥያቄ ውስጥ ከተዋል።

የናይጄሪያው ስጋት አማካሪ ድርጅት ኤስ ቢ ኤም ኢንተለጀንስ ለፈረንሳይ የዜና አገልግሎት እንደገለጸው ባለፈው አንድ አመት በመዲናዋ ቀጠና ዙሪያ ታፍነው የተወሰዱ 283 ሰዎችን መዝግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG