የጥምቀት ከተራ በዓል ከሌሎች አካባቢዎች በተለየ ድምቀት በሚከበርባት የጎንደር ከተማ፣ ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት በቁጥር እጅግ ያነሱ ተሳታፊዎችና ጎብኝዎች በተገኙበት እየተከበረ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል ።
ታቦታቱን ወደ ጊዜያዊ ማደሪያ በመሸኘት ላይ የነበሩ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ምዕመናን፣ “የዘንድሮው የከተራ በዓል ከወትሮው በተለየ የቀዘቀዘ ድባብ ታይቶበታል” ብለዋል።
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭትም ለተሳታፊዎች ቁጥር መቀነስ ምክንያት መሆኑን ነዋሪዎቹ ጠቅሰዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ቃል አቀባይ አቶ አበበ ላቀው ግን “በዓሉን ለማክበር በርካታ ዕንግዶች ወደ ከተማዋ ገብተዋል” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡
መድረክ / ፎረም