በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ የሁቲ ኢላማዎችን መደብደቧን ቀጥላለች


ፎቶ ፋይል፦ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን
ፎቶ ፋይል፦ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

በእስራኤል እና ሐማስ መካከል የሚካሄደው ጦርነት መካከለኛው ምሥራቅን ወደሚያጥለቀልቅ ጦርነት እንዳይሸጋገር በሚሰጋበት በዚህ ወቅት፣ የአሜሪካ ኃይሎች በኢራን በሚደገፉት ሁቲ አማፂያን ይዞታ ላይ ትናንት ሐሙስ ተጨማሪ ድብደባ ማድረጋቸው ተነግሯል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አገራቸው ድብደባውን እንደምትቀጥል ቢያስታውቁም፣ ሁቲዎች በቀይ ባሕር ላይ በሚመላለሱ መርከቦች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ግን አላቆሙም።

በአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስቴር መ/ቤት (ፔንታገን) ምክትል ቃል አቀባይ የሆኑት ሳብሪና ሲንግ ለዜና ሰዎች እንደተናገሩት፣ የሁቲ አማፂያኑ ሁለት ፀረ መርከብ ባሊስቲክ ሚስዬሎችን የአሜሪካ ንብረት ወደሆነው የነዳጅ መርከብ ላይ ለማስወንጨፍ በዝግጅት ላይ ሳሉ፣ የአሜሪካ ኤፍ 18 ተዋጊ ጄቶች አውድመዋቸዋል።

ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ አሜሪካ የመን ውስጥ በሚገኙ የሁቲ ኢላማዎች ላይ አምስት ግዜ ጥቃት መፈጸሟ ታውቋል።

ከትናንት በስቲያ ረቡዕ አሜሪካ ባደረገችው ድብደባ 14 የሁቲ ሚሳዬሎችን መምታቷን አስታውቃለች፡፡

ሚሳዬሎቹ ለመወንጨፍ ተዘጋጅተው ሳለ እንደተመቱ የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG