በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማ እና እዬኤል ስለ “የደጋ ሰው”


የማ እና እዬኤል ስለ “የደጋ ሰው”
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:52 0:00

የማ እና እዬኤል ስለ “የደጋ ሰው”

ድምጻዊት የማርያም ቸርነት በምድረክ ስሟ ‘የማ’ በድምጽ፣ የያሬድ ሙዚቃ ትምሕርት ቤት መምሕሩ እዮኤል መንግሥቱ ደግሞ በዝግጅት እና በቅንብር ያዋሃዱት የ ‘ደጋ ሰው’ የሙዚቃ አልበም፣የተለያዩ የሙዚቃ ባሕሎችን ያዛመደ አዲስ ሥራ ነው።

ከሰባት በላይ ትልልቅ ሙዚቀኞች የተሳተፉበትና ረዥም የዝግጅት ጊዜን የወሰደው የደጋ ሰው የሙዚቃ አልበም ተጠናቆ ሲለቀቅ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከባለሞያ እስከ አድማጭ ሙገሳን ተችሮታል።

አድናቆቱ በሙዚቃ ቅንብሩ፣ በአቀራረቡ፣ በግጥም እና ዜማው ብቻ ሳይኾን፤ ድምጻዊቷን ከአንጋፋዋ ኢትዮጵያዊት የሙዚቃ ሰው እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) ጋራ ያመሳሰሉ፤ የጂጂ ታናሽ ‘የጂጂ ደቂቅ’ የሚል ያደነቁም አሉ። የማ - አልበሙ በተለቀቀ በጥቂት ቀናት ውስጥ ያገኘችው ይህ አድናቆት እንከበዳት ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራት ቆይታ ተናግራለች።

‘የደጋ ሰው’ እጅግ ከምዕራብ አፍሪካው ኮራ እስከ ኢትዮጵያዊው ቱም እንዲሁም የአውሮፓ ሀገርና የሙዚቃ መሳሪያዎች ጥቅም ላይ የዋሉበት፤ ከሙዚቃ ቅንብሩ ለገበያ እስከዋለበት ጊዜ ድረስ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ የታየበት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለአልበሙ ማስታወቂያም ዘጋቢ ፊልሞች እና ለየት ያለ ድረገጽ የተዘጋጀለት ሲሆን፤ የአልበሙ የጀርባ አጥንት እዮኤል መንግስቱ ለአልበሙ ከወጣው የገንዘብ ዋጋ ይልቅ ትኩረት እንዲደረግ የሚሻው አልበሙን ልዩ በሚያደርጉት ነገሮች ላይ መሆኑን ይናገራል፡፡

የደጋ ሰው አልበም እንደ ዶ/ር እዝራ አባተ፣ ድራመር እዝራ በየነ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ ጆርጋ ስዩም፣ ይልማ ገ/አብ፣ እንድሪስ ሀሰን፣ ጋሞዎቹ እና ሌሎች የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ሙዚቀኞችን ያካተተ አካቷል።

በተጨማሪም አልበሙ ላይ ካሉት አስራ አንድ የሙዚቃ ስራዎች ስምንቱ የግጥም ስራዎች 'ጎላ ጎህ' የተሰኘ የብዕር ስም በተጠቀመ ግጥም ጸሃፊ የተጻፉ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG