“እስራኤላውያኑ ታጋቾች ወደ ቤታቸው ሳይመለሱ ጊዜው እየረፈደ ነው” በሚል ቤተሰቦቻቸው ስጋት አድሮባቸዋል።
አሁንም ድረስ ጋዛ ውስጥ እስር ላይ የሚገኙት 136 እስራኤላውያን ታጋቾች ጉዳይ አያሳሰበ ነው። በህይወት ወደ ቀያቸው ሊመለሱ የሚችሉበት ጊዜ ‘እያመለጠ ነው’ ሲሉም ቤተሰቦቻቸው እየወተወቱ ነው። ከሃማስ ጋር ሊደረስ የሚችል የትኛውም ስምምነት ለጋዛው ጦርነት ማብቂያ ሊያበጅ ይችላል። ይሁን እንጂ የእስራኤል መሪዎች “ያ አሁን አማራጭ አይደለም” ይላሉ።
ሊንዳ ግራድስቲን ከኢየሩሳሌም ለአሜሪካ ድምጽ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም