በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዐረብ ሊግ ዋና ጸሓፊ የኢትዮጵያንና ሶማሊላንድን ስምምነት አወገዙ


የዓረብ ሊግ ዋና ፀሓፊ የሆኑት አህመድ አቡል ጌት
የዓረብ ሊግ ዋና ፀሓፊ የሆኑት አህመድ አቡል ጌት

ኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ፣ በቅርቡ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታገኝ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን፣ የዐረብ ሊግ ዋና ጸሓፊ አሕመድ አቡል ጌት አውግዘዋል።

ዛሬ በተደረገው የዐረብ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባ ላይ፣ የመግባባቢያ ሰነዱ፥ “በዐረብ፣ በአፍሪካውያንና በዓለም አቀፍ መርሖዎች ላይ የተቃጣ ግልጽ ጥቃት ነው፤” ሲሉ፣ ዋና ጸሓፊው እንደተናገሩ፣ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

በዐረብ፣ በአፍሪካውያንና በዓለም አቀፍ መርሖዎች ላይ የተቃጣ ግልጽ ጥቃት ነው፤”

ስምምነቱ፥ የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንደሚጥስ በመንግሥቱ የተያዘውንም አቋም፣ የዐረብ ሊግ እንደሚደግፈው ዋና ጸሐፊው ማስታወቃቸውንና ቀጣናዊ ውጥረትንም እንደፈጠረ ማመልከታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

አሕመድ አቡል ጌት አያይዘውም፣ “በአገር ውስጥ ያሉ ያልተረጋጉ ሁኔታዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የሚወሰድን ማንኛውም ርምጃ እንዲከላከል” ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪ አድርገዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG