በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ከጦርነት የተረፉ ፈንጂዎችን ለማምከን የሚረዳ ጥናት ሊካሄድ ነው


በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የደህንነት ትብብር ቢሮ፣ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር የሰብዓዊ ፈንጂ ማምከን ማሰልጠኛ ማዕከል እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚስሪያ ቤት የጦር መሳሪያ ማስወገድ እና ቅነሳ ፕሮግራም ተወካዮች ከኢትዮጵያ መከላከያ ኃይሎች ጋር በመሆን ፕሮግራሙን ሲያስጀምሩ - ጥር 15፣ 2024
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የደህንነት ትብብር ቢሮ፣ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር የሰብዓዊ ፈንጂ ማምከን ማሰልጠኛ ማዕከል እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚስሪያ ቤት የጦር መሳሪያ ማስወገድ እና ቅነሳ ፕሮግራም ተወካዮች ከኢትዮጵያ መከላከያ ኃይሎች ጋር በመሆን ፕሮግራሙን ሲያስጀምሩ - ጥር 15፣ 2024

በመላው ኢትዮጵያ የጦርነት አውድማ በነበሩ አካባቢዎች የተቀበሩ ፈንጂዎች፣ ያልፈነዱ የመድፍ ጥይቶች እና ሌሎች ከጦርነት የተረፉ ተተኳሾች ዜጎች ላይ ድንገተኛ ሞት እያስከተሉ እና ገበሬዎች ወደ እርሻቸው እንዳይመለሱ እያደረጉ በመሆኑ፣ የዳሰሳ ጥናት ሊካሄድ መሆኑን በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ።

ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ያልፈነዱ የከባድ መሳሪያ ተተኳሾች መጠን ምን ያክል መሆኑን የሚለይ የዳሰሳ ጥናት ያስፈለገው፣ በኢትዮጵያ ከጦርነት የተረፉ ፈንጂዎች፣ የሰዎችን ደህንነት እና መተዳደሪያቸውን አደጋ ላይ እየጣሉ በመሆኑ እና ትጥቅ የማስፈታት እና የቀድሞ ታጋዮችን ወደ ማህበረሰቡ የማዋሃድ ሂደት እያስተጓጎሉ በመሆኑ ነው።

ጥናቱ የሚካሄደው የኤምባሲው የደህንነት ክፍል እና የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር፣ ከኢትዮጵያ ፈንጂ አምካኝ ጽህፈት ቤት ጋር በሚያደርጉት ትብብር መሆኑን ኤምባሲው ያወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ከአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር የሰብዓዊ ፈንጂ ማምከን ማሰልጠኛ ማዕከል እንዲሁም፣ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የጦር መሳሪያ ማስወገድ እና ቅነሳ ፕሮግራም የተውጣጡ ባለሞያዎች ከኢትዮጵያ ባለሞያዎች ጋር በመሆን ከጥር 6-10 ባለው የአንድ ሳምንት ጊዜ ጥናቱን እንደሚያካሂዱም ተገልጿል። በተጨማሪም ቡድኑ ትላንት ሰኞ ጥር 6፣ 2016 ዓ.ም ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን እና የኢትዮጵያ ፈንጂ አምካኝ ጽህፈት ቤትን መጎብኘታቸውን ኤምባሲው ገልጿል።

ከአሜሪካ የተውጣጡት ባለሞያዎች በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ የሚያደርጉት የዳሰሳ ጥናት፣ ከጦርነት የተረፉ ያልፈነዱ ተተኳሾችን መጠን ለመለየት እንደሚረዳ የገለፀው የኤምባሲው መግለጫ፣ የጥናቱ የመጨረሻ ግብ፣ ጉዳት በደረሰባቸው ክልሎች የሚኖሩ ሲቪሎችን ደህንነት እና የእርሻ ምርታማነት ማሻሻል መሆኑን አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG