በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በከፍተኛው የተመድ ዓለም አቀፍ ፍ/ቤት የተከሰሰችበትን የጋዛ የዘር ማጥፋት ክስ ተከላከለች


ምስሉ በሄግ፣ ኔዘርላንድስ በሚገኘው የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ችሎት ዳኞች እና ተሟጋቾች ስፍራቸውን ይዘው ያሳያል ።
ምስሉ በሄግ፣ ኔዘርላንድስ በሚገኘው የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ችሎት ዳኞች እና ተሟጋቾች ስፍራቸውን ይዘው ያሳያል ።

በፍልስጤማዊያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች በሚል የተከሰሰችው እስራኤል ፣ በጋዛ በማካሄድ ላይ ያለችው ጦርነት ህግን የተከተለ ፣ ህዝቦቿን ከጥቃት መከላከያ እርምጃ መሆኑን እንዲሁም በዘር ማጥፋት ወንጀል ጥፋተኛ የሆኑት የሀማስ ተዋጊዎች መሆናቸውን በመጥቀስ በተባበሩት መንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከራክራለች ።

በደቡብ አፍሪካ የቀረበባትን ክስ "ግብዝነት " ስትል የጠራችው እስራኤል ፣ ክሱ በዓለም አቀፉ የጦር ፍርድ ቤት ፊት ከቀረቡት እና የተገላባበጠ ዓለምን ከሚንጸባርቁ ክሶች መካከል አንዱ መሆኑን ተናግራለች ።


እስራኤላውያን መሪዎች በጋዛ የተደረጉ የአየር እና የምድር ጥቃቶች በአውሮፓዊያኑ ጥቅምት 7 በእስራኤል ማህበረሰቦች ላይ ታጣቂዎች ወረራ በመፈጸም 1,200 ሰዎችን ገድለው ወደ 250 የሚጠጉ ሰዎችን ላገቱበት የሀማስ ጥቃት የተሰጠ ህጋዊ ምላሽ ነው በማለት ይማገታሉ ።

የእስራኤል የህግ አማካሪ የሆኑት ታል ቤከር ዘሄግ በሚገኘው ፣ በታዳሚዎች በተሞላው ፣ የሰላም ቤተ-መንግስት በሚል በሚጠራው ያጌጠ ችሎት ፊት ተገኝተው ሀገራቸው ባልጀመረችው እና ባልፈለገችው ጦርነት ውስጥ እንደምትገኝ ተናግረዋል ።

"አሁን ባለው ሁኔታ ፣ በእስራኤል ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከቀረበበት ክስ የበለጠ ሐሰት እና ክፋት ሊኖር አይችልም” ሲሉ ያከሉት አማካሪው ፣ በጦርነት ወቅት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ አሰቃቂ ክስተቶች ይህን ክስ ለመመስረት በቂ አለመሆናቸውን ሊያስረዱ ጥረዋል ።

አርብ ከሰአት በኋላ ጀርመን በእስራኤል ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ለማቅረብ "ምንም ዓይነት መሰረት የለም" በማለት በእስራኤል ስም በሂደቱ ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደምትፈልግ ተናግራለች።
በፍርድ ቤቱ ህግ መሰረት ጀርመን በጉዳዩ ላይ የጣልቃ ገብነት ጥያቄ ካቀረበች እስራኤልን ወክላ ህጋዊ ክርክር ማድረግ ትችላለች።


የደቡብ አፍሪካ ጠበቆች የ 2.3 ሚሊዮን ፍልስጤማውያን መኖሪያ በሆነው፣ በከበባ ስር በሚገኘው የባህር ዳርቻ ግዛት የእስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲቆም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ሐሙስ ዕለት ጠይቀዋል። በዚህ ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ሳምንታት ሊወስድ ይችላል ። ሙሉ ጉዳዩን ለማየት ለዓመታት ሊቆይ በሚችለው የፍርድ ሂደት የሚሰጠውን ውሳኔ እስራኤል ስለ መቀበሏ ግልጽ አይደለም።(ዘገባው የአሶሼትድ ፕረስ ነው)

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG