በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ቀንድ ውሎና ትንታኔ


የአፍሪካ ቀንድ ውሎና ትንታኔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:02 0:00

የአፍሪካ ቀንድ ውሎና ትንታኔ

የሶማሊያው ፕሬዚደንት ሃሰን ሼክ ሞሃሙድ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ዛሬ እኩል ቀን አሥመራ ገብተዋል።

ፕሬዘዳንቱ ወደ ኤርትራ ከመሄዳቸው ከቀናት በፊትም ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ውድቅ የሚያደርግ ህግ ትናንት ፈርመዋል።

አፍሪካ ኅብረት፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ ዩናይትድ ኪንግደም እንዲሁም ሌሎችም ሃገሮችና ተቋማት አፍሪካ ቀንድ ላይ የተነሳውን ውዝግብ ለመፍታት የሚመለከታቸው ሁሉ ለዲፕሎማሲ ንግግሮች እንዲቀመጡ አሳስበዋል።

የባህር በር አልባዋ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የፈፀመችው ስምምነት 20 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የባህር ጠረፍ ለ50 ዓመታት እንድትከራይ፣ ለንግድና ለጦር መደብነትም እንድትጠቀምበት የሚፈቅድ ነው። ሶማሊላንድን “የግዛቴ አካል ነች” የምትለው ሶማልያ ግን ውሉን በብርቱ መቃወሟን ቀጥላለች።

የፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህን የትናንት እርምጃ አቅምና ተፈፃሚነት በሚመለከትና በሌሎችም የቀጣናው አክራሞት ላይ ተንታኔ ያካተተ ዘገባ ተያይዟል፤ ያዳምጡት።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG