በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የላቀ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች የሚያበርታቱት ባለሃብት


የላቀ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች የሚያበርታቱት ባለሃብት
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:03 0:00

የላቀ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች የሚያበርታቱት ባለሃብት

በኢትዮጵያ ከሰሞኑ የተጀመረው የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶችን በፌስቡክ ማህበራዊ የትስስር ገጽ የሚያሳትፍ የግል ተነሳሽነት ትኩረትን ስቧል፡፡

አቶ ቢጃይ ናይከር በተባሉ ኢትዮጵያዊ ባለሃብት የተጀመረው ይህ ተነሳሽነት ወጣቶቹ አዲስ ሥራ ለመጀመር የሚያስችል የፈጠራ ሃሳባቸውን በማኅበራዊ የትስስር ገጽ እንዲያጋሩ በማድረግ በእያንዳንዱ የውድድር ዙር ለተመረጠ ወጣት ለሥራ መጀመሪያ የሚሆን እስከ አንድ መቶ ሽህ ብር ድጋፍ የመስጠት ፕሮጀክት ነው፡፡

በራያ አላማጣ ከተማ የሚኖረው ወጣት አብዱ ሰላም ማሩፍ በመጀመርያው ዙር ውድድር የሥራ ሃሳቡን አቅርቦ በመመረጡ የሥራ ማስጀመርያ ገንዘብ ማግኘት መቻሉን ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጧል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ወ/ሮ ሃውለት አህመድ ይህ ተነሳሽነት ከተለመደው በፋይናንስ ተቋማት ከሚሰጡ የብድር ወይም የድጋፍ ዓይነቶች የተለየና የወጣቶችን የሥራ ተነሳሽነት ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG