በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአውሮፓ ህብረት ጦር እንዲቋቋም ጥሪ አቀረቡ


ፋይል - የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ በህዳር ወር ፓርላማ ውስጥ ለቀረቡላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ - ህዳር 23፣ 2023
ፋይል - የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ በህዳር ወር ፓርላማ ውስጥ ለቀረቡላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ - ህዳር 23፣ 2023

የአውሮፓ ህብረት፣ የሰላም ማስጠበቅ ሚና ያለው እና ግጭቶችን ለመከላከል የሚረዳ የራሱን ጥምር ጦር ሊመሰርት ይገባል ሲሉ የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ ጥሪ አቀረቡ።

ታጃኒ፣ ላ ስታምፓ ከተሰኘ የጣሊያን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በመከላከያ ረገድ የአውሮፓ ህብረት የተጠናከረ ትብብር መፍጠር፣ እሳቸው የሚመሩት ፎርዛ ኢታሊያ ፓርቲ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

"በዓለም ላይ ሰላም አስከባሪ መሆን ከፈለግን የአውሮፓ ጦር ያስፈልገናል" ያሉት ታጃኒ "ውጤታማ የአውሮፓ የውጭ ፖሊሲ እንዲኖረን ከተፈለገ ይሄ መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታ ነው" ማለታቸው እሁድ እለት በታተመው ጋዜጣ ላይ ተመልክቷል።

ታጃኒ አክለው "እንደ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ እና ሩሲያ ያሉ ኃያል ተጫዋቾች ባሉበት ዓለም እና፣ ከመካከለኛው ምስራቅ አንስቶ እስከ የህንድ ፓስፊክ ቀውሶች ባሉበት፣ የጣሊያን፣ የጀርመን፣ የፈንሳይ ወይም የስሎቫኒያ ዜጎች ሊጠበቁ የሚችሉት አስቀድሞ በተዘጋጀ የአውሮፓ ህብረት ብቻ ነው" ማለታቸውም ተገልጿል።

አውሮፓ የመከላከያ ትብብር እንዲኖረው የሚጠይቀው ሀሳብ፣ ከሁለት አመት በፊት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረገችውን ወረራ ተከትሎ እያደገ ቢመጣም፣ የበለጠ ትኩረት የተሰጠው ግን ለሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) መስፋፋት ነው።

የአውሮፓ ሀገር የሆነችው ፊንላንድ ባለፈው አመት ጥምረቱን ስትቀላቀል፣ ስዊድንም በቅርቡ ለመቀላቀል መንገድ ላይ ናት።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG