ቲክቶክ በኢትዮጵያ በወጣቶች ዘንድ ከጊዜ ወደጊዜ በይበልጥ እየተዘወተረ መምጣቱ ይስተዋላል ፡፡
ባለሙያዎች ታዲያ አጠቃቀሙን በተመለከተም ቲክቶክ ይዟቸው የመጣቸው ጠቀሜታዎች ቢኖሩም ጉዳቶቹ አመዝኗል በማለት ይተቻሉ፡፡
ከዚህ ሃሳብ ተጋሪዎች አንዱ የሆኑትና የህይወት ክህሎት ስልጠና ላይ የሚሰሩት አቶ ብርሃኑ ራቦ የቲክቶክ የትስስር ገጽ ሃሳብን በነጻነት የሚገለጽበት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ አብዛኞቹ ወጣቶች የሚያጋሯቸው ይዘቶች ማህበረሰባዊ እሴትን የሚሸረሽሩ እየሆኑ መጥተዋል ሲሉ ይተቻሉ፡፡
የስነ ልቦና ባለሙያው አቶ ያፌት ከፈለኝ በበኩላቸው ሁልጊዜም አዳዲስ የቴክኖሎጅ ውጤቶች ሲወጡ ጥቅምና ጉዳትን ይዘው እንደሚመጡ ገልጸው ቲክቶክም ከስነ ልቦና አንጻር ሲታይ በወጣቶች ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ እንዳለ ይናገራሉ፡፡
የዚህን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡
መድረክ / ፎረም