በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለምን ሪከርድ የሰበረ የአዲስ አመት ርችት እና የድሮን ትዕይንት በተባበሩት ኤሚሬትስ ተካሄደ


የፈረንጆቹ አዲስ አመት ዋዜማ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ
የፈረንጆቹ አዲስ አመት ዋዜማ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ

በፈረንጆቹ አዲስ አመት ዋዜማ፣ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ትላልቅ ከተሞች መካከል አንዱ በሆነው ራስ አል ካይማህ ከተማ፣ አንድ ሺህ ድሮኖችን በመጠቀም እና በውሃ ላይ በተነጠፈ የርችት ስነ-ስርዓት የተካሄደው የብርሃን ትዕይንት "በዓለም ረጅሙ የድሮን ትዕይንት" እና "ረጅሙ የውሃ ላይ ተንሳፋፊ ርችት" የሚሉ ስያሜዎችን አግኝቷል።

ለስምንት ደቂቃ የቆየው ይህ ትዕይንት 4.5 ኪሎሜትር በሸፈነ የባህር ዳርቻ ላይ የተካሄደ ሲሆን ከዚህ በፊት ተሞክሮ በማያውቅ መልኩ የተሰናዳ እና በልዩ ልዩ ዳንሶች የታጀበ ነበር። ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ትዕይንቱን ለማየት በመሰባሰባቸውም፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተመልካች እና አስደናቂ የቱሪዝም ስኬት ማስመዝገብ ችሏል።

ራስ አል ካይማህ ላለፉት አምስት አመታት ያልተለመደ የአዲስ አመት ዋዜማ አከባበር በማሳየት እውቅና ያገኘ ሲሆን በዓለም ላይ ተመራጭ የቱሪስ መዳረሻ ስፍራ እንዲሆን ረድቶታል። ሲ ኤን ኤን የቴሌቭዥን ጣቢያ እ.አ.አ 2023 መጎብኘት ካለባቸው ከተሞች አንዱ አድርጎ መርጦት ነበር። ከተማዋ ቱሪስቶችን ለመሳብ በሚያደርገው ጥረትም እ.አ.አ በ2030 ከሦስት ሚሊየን በላይ አመታዊ ጎብኚዎችን ለመሳብ እቅድ ተይዟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG