በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ጋዛን የመቆጣጠር ዓላማ እንዳላት ኔትኒያሁ ይፋ አደረጉበጋዛ ሰርጥ ደቡባዊ ራፋ የተፈናቀሉ የፍልስጤም ህጻናት በሰዓሊው አማል አቦ ከተሰራው የአደባባይ ስዕል አጠገብ ይታያሉ ።
በጋዛ ሰርጥ ደቡባዊ ራፋ የተፈናቀሉ የፍልስጤም ህጻናት በሰዓሊው አማል አቦ ከተሰራው የአደባባይ ስዕል አጠገብ ይታያሉ ።

በጋዛ ሰርጥ እና በግብጽ መካከል ያለው ድንበር አካባቢ ከጦር እንቅስቃሴ ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ በእስራኤል ቁጥጥር ስር ሊሆን እንደሚገባ ፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትኒያሁ ትናንት በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል ።

የእስራኤል -ሐማስ ጦርነት 13ኛ ሳምንቱን በያዘበት በአሁኑ ሰዓት በተሰማው ንግግራቸው ጦርነቱ ተጨማሪ ወራትን ሊወስድ እንደሚችልም ጠቁመዋል።

እስራኤል የድንበሩን ቀጠና ከተቆጣጠረች ፣በአውሮፓዊያኑ 2005 ዓም ከስፍራው የወጣችበትን ሂደት በመቀልበስ ለዓመታት በሐማስ እጅ ውስጥ የነበረውን የተነጠለ ስፍራ ዳግም በእጇ እንዲገባ ያደርጋል ።

"የፊላደልፊ መተላለፊያ- በትክክለኛው አጠራር ለማስቀመጥ ደቡባዊው የጋዛ ጫፍ -በእኛ እጅ ውስጥ ሊሆን ይገባል ፣ መዘጋት አለበት ።ሌላ አይነት አደረጃጀት የምንፈልገውን ከጦርነት ነጻ ቀጠና ሊያረጋግጥ አይችልም " ብለዋል ኔትኒያሁ ።

ኔትኒያሁ እስራኤል የፍልስጤም ግዛት ውስጥ ባደረገችው የጦር ዘመቻ 8000 ያህል ተዋጊዎች እንደተገደሉ ተናግረዋል ። በሐማስ የሚተዳደረው ጋዛ ግዛት የጤና ሚኒስትር ቅዳሜ ዕለት እንዳስታወቀው ፣ ጦርነቱ በጥቅምት ወር ከተቀሰቀሰ ወዲህ 21672 ሰዎች ተገድለዋል 56000 ያህሉ ደግሞ ለጉዳት ተዳርገዋል ። መግለጫው በሰላማዊ ሰዎች እና በተዋጊዎች መሐል ልዩነት አላስቀመጠም ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG