በምስራቅ ሶሪያ ከኢራቅ ጋር ስትራቴጂካዊ የድንበር ማቋረጫ አቅራቢያ ለሶስት ተከታታይ ሌሊቶች በተደረገ የአየር ድብደባ በኢራን የሚደገፉ ስድስት ታጣቂዎችን መገደላቸውን፤ ሁለት የኢራቅ ሚሊሻ ቡድን አባላት ለአሶሼትድ ፕሬስ የዜና አውታር ተናገሩ።
ቡካማል በተሰኘው ድንበር አካባቢ የተፈፀመው ጥቃት እስላማዊ ተቃውሞ በመባል የሚታወቀው እና በኢራን የሚደገፍ የኢራቅ ታጣቂዎች ስር ጥላ ስር ያለ ቡድች - በሰሜናዊ ኢራቅ ኢርቢል ከተማ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ማድረሱን ከገለጸ ከሰዓታት በኋላ ነው። በጎርጎርሳዊያኑ ጥቅምት ሰባት የሃማስ እና የእስራኤል ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቡድኑ በኢራቅ እና ምስራቅ ሶሪያ በሚገኙ የአሜሪካ ይዞታዎች ላይ ከመቶ በላይ ጥቃቶችን አድርሷል።
ከሟቾቹ ውስጥ አራቱ በሊባኖስ ሃያል የሆነው ሂዝቦላህ ቡድን አባላት ሲሆኑ፤ የተቀሩት ሁለቱ ሶሪያውያን መሆናቸውን ታጣቂዎቹ ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት ሁለቱ ግለሰቦች በጥቃቱ ተጨማሪ ሌሎች ሁለት ሰዎች ቆስለዋል ብለዋል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በአካባቢው የሚወጡ ዜናዎችን የሚዘበው ዴር ኤዞር 24 የተሰኘ የአክቲቪስቶች ኅብረት በአየር ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ሁለት ማዕከሎች በቅርቡ በሮኬት ማስወንጨፊያዎችና ጥይቶች የተከማቹባቸው ስፍራዎች መሆናቸውን ጠቁሟል።
በተጨማሪም ጥቃቱ ሶስት ሶሪያዊያንን እና ስድስት የሌላ ሀገር ዜጎችን ህይወት ቀጥፏል ሲል በዘገባው አስታውቋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ከዋሽንግተን የተሰማ ምላሽ ባይኖርም አንዳንዶቹ ጥቃቶች ባለፉት ሁለት ወራት በኢራን የሚደገፉ ሚሊሻዎችን ዒላማ ያደረጉ እንደነበሩ አስታውቋል።
ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ሳምንት የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሰራዊት ሥስት የየዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ላይ ጥቃት በፈጸሙ በኢራን የሚደገፉ የኢራቅ ቡድኖች ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ ማዘዛቸው የሚታወስ ነው።
መድረክ / ፎረም