በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዲሱ የፈንጆች ዓመት 'መተማመን እና ተስፋ' እንዲጎለብት የተመድ ዋና ፀሃፊ አሳሰቡ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ለአዲሱ ዓመት ባስተላለፉት መልዕክታቸው በዚያ ሳምንት የሚያበቃው የአውሮፓውያኑ 2023 ዓመት "በከፍተኛ ስቃይ፣ ብጥብጥ እና የአየር ንብረት ቀውስ የተሞላ ዓመት ነበር” ሲሉ ተናገሩ፡፡

መጭው “2024 በጋራ ልናሳካቸው የሚገቡ ተግባራትን ለማከናወን መተማመን እና ተስፋ የምንገነባበት ዓመት ሊሆን ይገባል” ሲሉም አሳስበዋል፡፡ ዋና ጸሀፊው አክለው፣ አስቀድሞ በተቀረጸ የቪዲዮ መልዕክታቸው፣ “ሰብአዊነት ስቃይ ውስጥ ነው፣ ዓለማችን አደጋ ውስጥ ናት” ሲሉ በዓለም ዙሪያ እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶችን አስታውሰዋል።

“2023 እጅግ ሞቃታማ ዓመት ሆኖ የተመዘገበ ነበር” ያሉት ጉተሬዥ “ሰዎች እያደገ በመጣው ድህነትና ረሃብ እየተደቆሱ ነው፡፡ ጦርነቶችም በቁጥር እና በአስከፊነታቸው በርክተዋል” ብለዋል።

“ይሁን እንጂ ግን ጣት መቀሰር እና ጠመንጃ የትም አያደርሱም” ያሉት የተመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ፣ “ሰብአዊነት በጣም ጠንካራ የሚሆነው በአንድ ላይ ስንቆም ነው” የሚለውን መልዕክት ያጎሉ ሲሆን፣ ዓለም በሀገራት እና በማህበረሰቦች መካከል መርዝ እየረጨ ነው ያሉትን ጥላቻ እና ማግለል ለማስወገድ አብሮ እንዲቆምም ጠይቀዋል። የመንግስታቱ ድርጅት ለዓለም ሰላም፣ ለዘላቂ ልማት እና ለሰብዓዊ መብት መታገሉን እንደሚቀጥልም አስረግጠው በመናገርም መልካም አዲስ ዓመት ተመኝተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG