በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካውያን ቤተሰቦቻቸውን ከጋዛ ለማውጣት እርዳታ እየጠየቁ ነው


መቼ እንደተነሳ ጊዜው ያልተገለፀው ፎቶ ፋዲ ሻክ ከቤተሰቦቹ ጋር የተነሳውን ፎቶ ያሳያል። በስተግራ የሚታዩት አባቱ አብደላ ሻክ በጋዛ በተካሄደ የቦምብ ጥቃት ባለፈው ወር ተገድለዋል። የ56 አመት እናቱ ደግሞ ከልጆቻቸው ቀጥለው በስተቀኝ ይታያሉ።
መቼ እንደተነሳ ጊዜው ያልተገለፀው ፎቶ ፋዲ ሻክ ከቤተሰቦቹ ጋር የተነሳውን ፎቶ ያሳያል። በስተግራ የሚታዩት አባቱ አብደላ ሻክ በጋዛ በተካሄደ የቦምብ ጥቃት ባለፈው ወር ተገድለዋል። የ56 አመት እናቱ ደግሞ ከልጆቻቸው ቀጥለው በስተቀኝ ይታያሉ።

በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ አሜሪካውያን ቤተሰቦቻቸውን ከጋዛ ማውጣት እንዲችሉ ከባይደን አስተዳደር እና ከዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት እርዳታ እየጠየቁ ነው።

የጋዛ ጤና ሚኒስትር እንዳስታወቀው እስካሁን በጦርነቱ ከ20 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ከ53 ሺህ 600 በላይ ደግሞ ቆስለዋል የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ከግማሽ ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ጋዛ ውስጥ ለረሃብ መጋለጣቸውን አስታውቋል።

በቦምብ ጥቃት አባቱን ጋዛ ውስጥ ያጣው እና እናቱን ለማውጣት እየጣረ ያለው የ25 አመት ወጣት ፋዲ ሻክ፣ ላለፉት ስድስት ቀናት ከቆሻሻ ፍሳሽ የሚወርድ ውሃ እየጠጡ በህይወት የቆዩትን እናቱን ማየት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

አንዳንድ የአሜሪካ ዜጎች እና ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ጋዛ አቅራቢያ በሚገኘው እና ወደ ግብፅ መሸጋገሪያ በሆነችው ራፋህ ከተማ መውጫ አጥተው የሚገኙ ሲሆን፣ ጋዛን ለቀው ለመውጣት የሚያስችላቸው የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የሚያዘጋጀው የስም ዝርዝር ውስጥ ለመግባት በተስፋ እየተጠባበቁ እየተጠባበቁ ነው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አርብ እለት ባወጣው መግለጫ ከ1ሺህ 300 በላይ የአሜሪካ ዜግነት እና ህጋዊ መኖሪያ ያላቸውን ሰዎች ከነቤተሰቦቻቸው በራፋህ በኩል ወደ ግብፅ እንዲወጡ መርዳቱን አስታውቋል። የአሜሪካን እርዳታ የሚጠባበቁ የሌሎች 300 ሰዎችን ጉዳይ እየተከታተለ እንደሆነም ገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG