በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን በጋዛ ምክንያት የሜድትራኒያን ባህር ሊዘጋ እንደሚችል አስጠነቀቀች


የሁቲ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ያህያ ሳሬ በቀይ ባህር በሁለት የንግድ መርከቦች ላይ ስለደረሰው ጥቃት፣ እኤአ ታህሳስ 15 ቀን 2023 በዋና ከተማዋ ሰነዓ ለጋዛ ህዝብ አጋርነትን ለመግለጽ በተደረገው ሰልፍ ላይ መግለጫ ሲሰጡ።
የሁቲ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ያህያ ሳሬ በቀይ ባህር በሁለት የንግድ መርከቦች ላይ ስለደረሰው ጥቃት፣ እኤአ ታህሳስ 15 ቀን 2023 በዋና ከተማዋ ሰነዓ ለጋዛ ህዝብ አጋርነትን ለመግለጽ በተደረገው ሰልፍ ላይ መግለጫ ሲሰጡ።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ በጋዛ እየሰሩ ያሉትን ወንጀል የሚቀጥሉበት ከሆነ የሜዲትራኒያን ባህር ሊዘጋ ይችላል ማለታቸውን ታስኒም የተባለው የኢራን ዜና አገልግሎት ዛሬ ቅዳሜ ዘግቧል፡፡ ያ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ግን ዜና አገልግሎቱ ዝርዝሩን አልገለጸም፡፡

የኢራን ጦር ኃይል ከፍተኛ አዛዥ የሆኑት ብርጋዴር ጀነራል መሀመድ ሬዛ ናቅዲ የሜዲትራኒያን ባህር እና ጅብራልታር የሚባለውን የባህር ሰርጥ ጨምሮ ሌሎች የባህሩ መተላለፊያዎች “በቅርቡ ይዘጋሉ ብለው እንደሚጠብቁ” መናገራቸውንም ታስኒምን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ኢራን ከእስራኤል ላይ ጋር እየተፋለመ የሚገኘውን ሃማስን ትደግፋለች፡፡ በጋዛ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱትበትን፣ በርካቶች ከቤታቸው የተፈናቀሉበት እና ኢራን የእስራኤል ወንጀሎች ስትል የምትጠራውን ለሳምንታት የዘለቀውን የቦምብ ድብደባ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ትደግፋለች ስትልም ትከሳለች፡፡

በየመን ከኢራን ጋር የተቆራኘው የሁቲ ቡድን እስራኤል በጋዛ ላይ ላደረሰችው ጥቃት የበቀል እርምጃ በመውሰድ፣ ባለፈው ወር በቀይ ባህር አቋርጠው የሚጓዙ የንግድ መርከቦችን ሲያጠቃ ቆይቷል፡፡ አንዳንድ የመርከብ ድርጅቶችም የሚጓዙበትን አቅጣጫ እንዲቀይሩ ማድረጉ ተመልክቷል፡፡

ዋይት ሐውስ ትናንት ዓርብ ባወጣው መግለጫ፣ በቀይ ባህር ላይ የሚጒዙ የንግድ መርከቦችን በማጥቃቱ ዘመቻ እቅድ ኢራን በ”ጥልቀት ተሳትፋለች” ብሏል፡፡

ምንም እንኳ ናቅዲ የባህር መተላለፊያውን መዝጋት የሚችሉ አዲስ የተቋቁሞ ኃይሎች መፈጠራቸውን ቢናገሩም፣ ኢራን ከሜዲትራንያን ባህር ጋር በቀጥታ አትዋሰንም፡፡ በመሆኑም አብዮታዊ ዘቡ ቀይ ባህርን እንዴት አድርጎ የባህሩን በር ለመዝጋት እንዳሰበ ግልጽ አይደለም ሲል የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ "ትናንት የፋርስ ባህረ ሰላጤ እና የሆርሙዝ ሰርጥ ለእነሱ ቅዠት ሆነዋል፣ ዛሬም እንዲሁ በቀይ ባህር ከወጥመድ ውስጥ ገብተዋል” ሲሉ ናቅዲ ተናግረዋል፡፡

በሜዲትራኒያን ባህር አካባቢ በኢራን የሚደገፉ ብቸኞቹ ቡድኖች፣ ከባህሩ ሌላኛው ጫፍ ላይ የሚገኙት፣ የሊባኖስ ሂዝቦላህ እና በሶሪያ የሚገኘው የኢራን አጋር ሚሊሻ ብቻ መሆናቸውን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG