በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ተወላጅ የቀድሞ የመከላከያ አባላት በፋኖ ታጣቂዎች ከእስር ነጻ እንደወጡ ተናገሩ


የትግራይ ተወላጅ የቀድሞ የመከላከያ አባላት በፋኖ ታጣቂዎች ከእስር ነጻ እንደወጡ ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:22 0:00

የትግራይ ተወላጅ የቀድሞ የመከላከያ አባላት በፋኖ ታጣቂዎች ከእስር ነጻ እንደወጡ ተናገሩ

በዐማራ ክልል በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዳንግላ ከተማ ታስረው ከቆዩበት እስር ቤት፣ በፋኖ ታጣቂዎች ነጻ እንደወጡ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ የትግራይ ተወላጆች፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

ከ18 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ ተፈርዶባቸው እንደነበር የገለጹት ተወላጆቹ፣ የታሰሩትም “በማንነታችን የተነሣ ነው፤” ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የዐማራ ክልል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን በበኩላቸው፣ ከዳንግላ ከተማ ማረሚያ ቤት ያመለጡ ታራሚዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፣ ድርጊቱም፣ “ሕገ ወጥ” ሲሉ በጠሯቸው ቡድኖች እንደተፈጸመ ገልጸዋል፡፡

ለትግራይ ተወላጅ የፖለቲካ እስረኞች የሕግ ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመው የጠበቆች ቡድን አስተባባሪ ደግሞ፣ በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ከነበረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋራ በተገናኘ፣ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ እስረኞች፣ የዳንግላ ከተማን ጨምሮ በመላ አገሪቱ መኖራቸው እንደሚያውቅ ለአሜሪካ ድምፅ አመልክቷል።

ከኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG