በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዐዲስ ሰብሳቢ ተሾመለት


ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ
ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ከአምስት ወራት በፊት በገዛ ፈቃዳቸው ከሥልጣናቸው በለቀቁት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ምትክ፣ ዐዲስ ሰብሳቢ ተሾመለት።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ዛሬ ማክሰኞ ባካሔደው መደበኛ ስብሰባ፣ ወሮ. ሜላተወርቅ ኀይሉን፣ የምርጫ ቦርዱ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል።

ቦርዱ ሹመቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፣ ዐዲስ የተሾሙት ወሮ. ሜላተወርቅ ኀይሉ፣ ቀደም ብሎም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጽሕፈት ቤት ሓላፊ በመኾን፣ ከየካቲት 2012 ዓ.ምእስከ የካቲት 2015 ዓ.ም. እንዳገለገሉ ገልጿል።

ከዚኽ ቀደም፣ ቦርዱን በሰብሳቢነት ሲመሩ የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ከነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በገዛ ፈቃዳቸው ሥራቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ፣ ከአራት ወራት በላይ ቦታው ክፍት ኾኖ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG