ቀይ ባሕር ላይ በሚተላለፉ የንግድ መርከቦች ላይ የየመን ሁቲ ታጣቂዎች የሚያደርሱት ጥቃት በአንዳንዶቹ የንግድ መርከብ ኩባኒያዎች እና ግዙፎቹን የነዳጅ ኩባኒያዎች ላይ ስጋት አድሯል፡፡
በዚህም የተነሳ የዐለም አቀፍ ንግድ እንቅስቃሴዎች ለሸቀጦች እና ለነዳጅ አቅርቦቶች ወሳኝ በሆነው መተላለፊያ መጠቀም እየተዉ በመሆኑ የአቅርቦቶች መዘግየት እና የዋጋ መናር እንደሚከተል ይጠበቃል፡፡
ግዙፉ የነዳጅ ኩባኒያ ቢፒ ማናቸውንም የነዳጅ አቅርቦቶቹን በቀይ ባሕር በኩል ማጓጓዙን ለጊዜው ለማቆም መወሰኑን ትናንት አስታውቋል፡፡
በኢራን የሚታገዙት ሁቲ ታጣቂዎች ጥቃት በገበያው ላይ በፈጠረው ስጋት የተነሳ የነዳጅ ዋጋ በከፊል አሻቅቧል፡፡
መድረክ / ፎረም