በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጊኒ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ፍንዳታ ስምንት ሰዎች ሞቱ


በጊኒ መዲና፣ ኮናክሪ በሚገኝ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ላይ ዛሬ ሰኞ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ ስምንት ሰዎች ሲሞቱ፣ 84 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።

ፍንዳታውን ተከትሎ በሥፍራው የነበሩ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች በፀጥታ ኃይሎች ታጅበው ሲወጡ ተስተውሏል።

ፍንዳታው በአካባቢው የሚገኙ ቤቶችን የመስኮት መስታወት ሲያረግፍ፣ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው እንዲሸሹ አድርጓል ተብሏል።

የእሳት አደጋ ሠራተኞች እሳቱን በቁጥጥር ሥር ቢያውሉትም፣ ከባድ ጭስ እና እሳት በአካባቢው መታየት መቀጠሉን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

የእሳቱ መነሻ አልታወቀም ያለው የመንግስት መግለጫ፣ ምርመራ እንደሚደረግ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG