ከታሳሪዎቹ መካከል፣ የአቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአቶ ዮሐንስ ቧ ያለውን ጨምሮ፣ በማኅበራዊ የትስስር ገጾች እየተዘዋወሩ ካሉ የሦስት ግለሰቦች ፎቶግራፎች ላይ ካስተዋሉት ኹኔታ በመነሣት፣ የታሳሪዎቹ ደኅንነት እንደሚያሳስባቸው፣ ከጠበቆቻቸው አንዱ ሰሎሞን ገዛኸኝ አመልክተዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መርማሪ ቦርድ፣ የታሳሪዎቹን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በጥብቅ ሊከታተል እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ ከቦርዱ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡ የታሳሪ ቤተሰቦችም ተመሳሳይ ስጋታቸውን ገልጸው፣ ጉዳዩን ለኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳሳወቁ ተናግረዋል፡፡
ኢሰመኮ በበኩሉ፣ ታሳሪዎቹን በድጋሚ ለመጎብኘት ጥረት እያደረገ እንደኾነ አስታውቋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።